​ሦስት ረዳት ዳኞች የእግድ ውሳኔ ተወስኖባቸዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]


በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ሦስት ሳምንታት ጨዋታዎች ላይ ጥፋት ፈፀመዋል በተባሉ ሦስት ረዳት ዳኞች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ሀዋሳ ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ጥፋት ፈፅመዋል በተባሉ ዳኞች ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉ እንዲሁም በማስጠንቀቂያ የታለፉ ዳኞች መኖራቸው ይታወሳል፡፡ ከቀናቶች በፊት በድሬዳዋ ተከናውኖ በተጠናቀቀው የመጨረሻ ሦስት ጨዋታዎች ላይ ግብ ተቆጥሮ ከጨዋታ ውጪ በማለት የተዛባ ውሳኔ ሰጥተው በነበሩ ሦስት ረዳት ዳኞች ላይ ደግሞ አሁን ተመሳሳይ የቅጣት ውሳኔ ተወስኗል።

ወልቂጤ ከተማ ከሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ ላይ በሀይሉ ተሻገር ለወልቂጤ ከተማ ግብ ካስቆጠረ በኋላ ከጨዋታ ውጪ በማለት ግቧን የሻሯት እና ረጅም አመታትን ያገለገሉት ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው እና 1ለ1 በተጠናቀቀው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቸርነት ጉግሳ አማካኝነት ጎል አስቆጥሮ ግቧ ከጨዋታ ውጪ ናት በማለት የሻሯት ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ እንዲሁም ሰበታ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር አንድ አቻ ሲለያይ ፍፁም ገብረማርያም ተቀይሮ ገብቶ ለሰበታ ሁለተኛ ጎል አስቆጥሮ ፌዴራል ረዳት ዳኛ ደረጄ አመራ ከጨዋታ ውጪ ነች ብለው በመሻራቸው (ይህ ዳኛ ስህተት ከሰራም በኋላ ውድድሩ እስከ ሚያልቅ የዳኛ ሲሆን ሌሎቹ ግን ስህተቱን በሰሩ በማግስቱ መሸኘታቸው ልብ ይሏል) እያንዳንዳቸው የስድስት ወራት የእገዳ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡