ቅዱስ ጊዮርጊስ የግራ መስመር ተከላካይ አስፈረመ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ፈረሰኛቹ የግራ መስመር ተከላካይ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎችን ያለሽንፈት በመጓዝ በሊጉ አናት ወደ ዕረፍት ያመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በሁለተኛው ዙር ቡድናቸውን ለማጠናከር ከሰሞኑ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የተለያየውን የግራ መስመር ተከላካይ ያሬድ ሀሰንን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል፡፡

የቀድሞው የወልድያ ፣ መቐለ 70 እንደርታ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሰበታ ከተማ ተጫዋች ዘንድሮ በዓመቱ መጀመሪያ አዲስ አበባ ከተማን በመቀላቀል በክለቡ ቆይታ የነበረው ሲሆን ከሰሞኑ ከክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየት ማረፊያውን ቅዱስ ጊዮርጊስ አድርጓል፡፡

ያጋሩ