[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ከሰሞኑ ዋና አሰልጣኝ መሾሙን ያሳወቀው ድሬዳዋ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ እና ቡድን መሪውን ይፋ አድርጓል፡፡
ደካማ የውድድር ጉዞን በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር በማድረጉ ቀደም ብሎ ዋና አሰልጣኙ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን በመቀጠል ከቀናቶች በፊት ጊዜያዊ ረዳት አሰልጣኝ እና ረዳቶቹን (ከግብ ጠባቂው አሰልጣኝ አምባዬ በፍቃዱ ውጪ) ማሳበቱን ከገለፀ በኋላ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ድሬዳዋ ከተማ አዲስ ረዳት አሰልጣኝ እና ቡድን መሪ አሳውቋል፡፡
በረዳት አሰልጣኝነት የተመረጡት የቀድሞው የሐረር ካራማራ ቡድን እና ምድር ባቡር ተጫዋች በኋላም የምድር ባቡር አሰልጣኝ እና ቡድን መሪ በቅርብ ዓመታት ደግሞ የድሬዳዋ ከተማ የሴቶች ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ሆነው የሰሩት ዓለምሰገድ ወልደማርያም ሲሆኑ በቡድን መሪነት ደግሞ ድሬዳዋን በአሰልጣኝነት ከዛም ባለፈ ሰበታ ከተማን እና መተሃራ ስኳርን ያሰለጠኑትን ኃይሉ ግዛው መመደቡን ክለቡ አሳውቋል፡፡