​የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውላቸው ተራዝሟል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

👉”ይሄ ውል የሚያዝናናኝ አይደለም” አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል

👉”አሠልጣኝ ፍሬው ቡድኑን ከያዘ በኋላ የነበረው እድገት ምን ይመስላል የሚለውን ሥራ አስፈፃሚው ገምግሟል” አቶ ባህሩ ጥላሁን

ያለፉትን ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን በአሠልጣኝነት ሲመሩ የነበሩት አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ከወራቶች በፊት ውላቸው ማለቁ ይታወቃል። ምንም እንኳን አሠልጣኙ ውላቸው ቢያልቅም ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ከፌዴሬሽኑ ጋር ውል አስረው በሥራ ገበታቸው ላይ የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን በብዙሃን መገናኛ ፊት የሁለት ዓመት ውል ፈርመዋል።

አሠልጣኙ ከፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ ጋር ውሉን ከፈረመ በኋላ ስለስምምነቱ ገለፃ መደረግ ተጀምሯል። በቅድሚያም ዋና ፀሐፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተወል።
“ውሉ በይፋ ባይገለፅም ከዚህ ቀደም ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ተፈራርመን ወደ ስራ ገብተን ነበር። አሠልጣኝ ፍሬው ቡድኑን ከያዘ በኋላ የነበረው እድገት ምን ይመስላል የሚለውን የኢትትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ገምግሟል። በተለይ የምስራቅ እና መካከለኛው ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍ ማድረግ ችሏል። በዚህም ፌዴሬሽኑ ደስተኛ ነዉ። ከዚህ በተጨማሪ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድሮችን እያደረግን ነው። ውጤታማ መሆንም ችሏል። ፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም ለሴቶች አሰልጣኞች የሚሰጠው ውል አጫጭር ነበር። 3 ወር ከዛ 6 ወር ነበር። ይህ ስራ አስፈፃሚ ከመጣ ደግሞ ውሎችን 1 ዓመት አድርጓል።” ካሉ በኋላ አሁን ለአሠልጣኝ ፍሬው የተሰጠው ሁለት ዓመት እንደሆነ ተናግረዋል።

ፀሐፊው ጨምረው አሠልጣኙ የደሞዝ ማሻሻያ ተደርጓላቸው የተጣራ 50 ሺ ብር እንደሚያገኙ አመላክተዋል። በተጨማሪም ውድድር በማይኖርበት ጊዜ ከቴክኒክ እና ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የተለያዩ የልማት ስራዎችን እንደሚሰሩ ጠቅሰዋል።

በመቀጠል ደግሞ ውላቸው የተራዘመላቸው አሠልጣኝ ተከታዩን አጭር ሀሳብ በስፍራው ለተገኙ የብዙሀን መገናኛ አባላት አጋርተዋል። “ወደ ስልጠናው ዓለም ስገባ ትልቁ ራዕዬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠን ነበር። ቡድኑን ይዤ ሁለት ዓመት ሆኖኛል። በቆይታዬም የተለያዩ ስራዎችን ሰርተናል። ወደ ብሔራዊ ቡድኑ መምጣት ባለብኝ ሰዓት መጥቻለው ብዬ አላስብም። የሆነው ሆኖ መጀመሪያ ለ3 ወር ነበር ውሉ የተሰጠኝ። የብሩንዲን ቡድን ካሸነፍን በኋላ ውድድሩ በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ ነበር። ከዛ 6 ወር ፈረምኩ። በድጋሜም ተቋረጠ። በመቀጠል ለ1 ዓመት ፈርሜ ውድድሩን ቀጥያለው። ከዛ በሴካፋ ተሳትፈን መጥተናል። እንደተባለው ውሌ ካለቀ በኋላ ከፌደሬሽኑ ጋር ተነጋግሬ ውሌ ተራዝሟል። ይሄ ውል የሚያዝናናኝ አይደለም። አሁን ከሰራሁት በላይ የምሰራበት እንደሚሆን አስባለው።”

ያጋሩ