[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በዘንድሮው የውድድር ዓመት የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረ የውጪ ተጫዋች የሆነው አጥቂ ከጦሩ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።
ከሁለት ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተመለሰው መከላከያ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው የመጀመሪያ ዙር ውድድር 18 ነጥቦችን በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ይታወቃል። የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ በኋላም አሚኑ ነስሩ፣ ምንተስኖት አዳነ እና እስራኤል እሸቱን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው ክለቡ ከደቂቃዎች በፊት ከጋናዊው አጥቂ ኦኩቱ ኢማኑኤል ጋር በስምምነት ተለያይቷል።
በጋና አክራ የተወለደው ኦኩቱ አብዛኛውን የእግር ኳስ ህይወቱን በዛምቢያ ያሳለፈ ሲሆን ለካብዌ ዋሪየርስ፣ ዛናኮ እና ለብዩልድኮን ክለቦችም ግልጋሎት ሰጥቶ ማሳለፉ ይታወቃል። ተጫዋቹ ክረምት ላይ በጦሩ ቤት ለአንድ ዓመት ለመጫወት ፈርሞ የነበረ ቢሆንም አሁን በስምምነት መለያየቱን አረጋግጠናል። ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር የተለያየበት ምክንያት ደግሞ ጉልበቱ ላይ ጉዳት አስተናግዶ ክለቡ ቀዶ ጥገና እንዲያደርግ ጠይቆት ፍቃደኛ ባለመሆኑ እንደሆነ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።