[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ሲጀምሩ ለገጣፎ በጊዜያዊነት መሪነቱን የተረከበበትን ድል አስመዝግቧል። ኮልፌ እና ሰንዳፋም አሸንፈዋል።
ረፋድ 4፡00 ላይ ቂርቆስ ክ/ከተማን የገጠመው ሰንዳፋ በኬ 2-0 ማሸነፍ ችሏል። ለረጅም ደቂቃዎች ያለጎል በዘለቀው ጨዋታ ቅዱስ ተስፋዬ 6ኛው ደቂቃ ላይ ሰንዳፋን ቀዳሚ ሲያደርግ ዘኪ አብዱ 84ኛው ደቂቃ ላይ ሁለተኛውን አክሏል። ድሉን ተከትሎም ሰንዳፋ በኬ ወደ 6ኛ ከፍ ሲል ደካማ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ቂርቆስ የመጨረሻውን ደረጃ ይዟል።
8፡00 ላይ ለገጣፎ ለገዳዲ ከካፋ ቡና ያደረጉት ጨዋታ በለገጣፎ 2-1አሸናፊነት ተጠናቋል። ካፋ ቡና በታከለ ታንቱ የ13ኛ ደቂቃ ጎል ለረጅም ደቂቃዎች 1-0 መምራት ቢችልም የኋላ ኋላ ለለገጣፎ እጅ ተሰጥቷል። ድንቅ አቋም ላይ የሚገኘው ልደቱ ለማ በ82ኛው ደቂቀ ኣየአቻነቷን ጎል ሲያስቆጥር በ90ኛው ደቂቃ ኪሩቤል ወንድሙ ለገጣፎን ወሳኝ ሦስት ነጥብ ያስጨበጠች ወሳኝ ግብ አስቆጥሯል። ድሉን ተከትሎ ለገጣፎ ነገ ጨዋታውን የሚያደርገው ቤንች ማጂ ቡናን በመቅደም በ28 ነጥቦች ምድቡን መምራት ጀምሯል። ካፋ ቡና በአንፃሩ ባለበት 8ኛ ደረጃ ላይ ረግቷል።
በዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ኮልፌ ቀራኒዮ ከመሪዎቹ ተርታ የተጠጋበትን ድል ቡታጅራ ከተማ ላይ አስመዝግቧል። 2-0 በተጠናቀቀው ጨዋታ የኮልፌን ጎሎች በ12ኛው ደቂቃ ረጂብ ሚፍታህ እና በ84ኛው ደቂቃ ሙሉቀን ወንድሙ ማስቆጠር ችለዋል። ኮልፌ ዛሬ ያሸነፈው ቡታጅራን በግብ ልዩነት በልጦ ወደ 4ኛ ከፍ ሲል በተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደው ቡታጅራ ወደ 5ኛ ተንሸራቷል።