አዲስ አበባ ከተማ ረዳት አሰልጣኙን አሳውቋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተካፋይ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ ረዳት አሰልጣኙን ይፋ አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ እየተሳተፈ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ በአሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር መሪነት ዓመቱን ቢጀምርም አሰልጣኙ ከቡድን መሪው ጋር በፈጠሩት እሰጥ አገባ ከክለቡ ጋር በመለያየታቸው በረዳት አሰልጣኙ ደምሰው በፍቃዱ ሲመራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የሊጉ የጨዋታ ሳምንታት ሊገባደዱ ሁለት መርሀግብር ሲቀር ደምሰው በፍቃዱን የዋና አሰልጣኝነት መንበር መስጠቱም አይዘነጋም። ክለቡ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ወንዶች ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ከዚህ ቀደም በረዳት አሰልጣኝነት ያሰለጠኑት አሳምነው ገብረወልድን የምክትል አሰልጣኝነት ሚናን ሰጥቷል፡፡

አሰልጣኙ በቅዱስ ጊዮርጊስ የወጣት ቡድን እንዲሁም ያለፉትን ሦስት ዓመታት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ሆነው ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል።

ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በተያያዘ ሌላ ዜና 18 ቀናት በኋላ በአዳማ ከተማ ለሚጀመረው የሁለተኛ ዙር የሊጉ ውድድር ከቀሪ ተወዳዳሪዎች ቀድሞ በትናንትናው ዕለት ወደ ከተማዋ ማቅናቱ ታውቋል።