የከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ 14ኛ ሳምንት ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ውሎ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 14ኛ ሳምንት ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ሲከናወኑ ቡራዩ ከተማ እና ቤንች ማጂ ቡና ወሳኝ ድል አስመዝግበዋል።

ስምንት ሰዓት ላይ ከንኣታ ሺንሺቾን የገጠመው ቡራዩ ከተማ 2-1 በማሸነፍ ወደ ምድብ መሪነቱ ተመልሷል። ቡራዩ ጫላ በንቲ በ18ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ቀዳሚ መሆን ሲችል ከእረፍት በኋላ ይሁን ደጀኔ 63ኛው ደቂቃ ላይ ሺንሺቾን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። ሆኖም 72ኛው ደቂቃ ላይ መለሰ ሚሻሞ ቡራዩን እጅግ ወሳኝ ሦስት ነጥብ ያስገኘች ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በቡራዩ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ድሉን ተከትሎ ትናንት ለገጣፎ በማሸነፉ መሪነቱን ተነጥቆ የነበረው ቡራዩ ከተማ በግብ ልዩነቶች በመብለጥ ወደ መሪነቱ ተመልሷል።

10፡00 ላይ በሁለተኛው ዙር ግሩም መሻሻል ያሳየው ቤንች ማጂ ቡና ስልጤ ወራቤን ገጥሞ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረ ጎል ከመሪዎቹ ጋር ያለውን ልዩነት ያስጠበቀበትን ድል አስመዝግቧል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ጎል በዘለቀው ጨዋታ ጭማሪ 4ኛ ደቂቃ ላይ ጌታሁን ገላዬ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሮ አቦሎቹ 1-0 ማሸነፍ ችለዋል። ድሉን ተከትሎ ቤንች ማጂ ቡና ነጥቡን 25 በማድረስ ከመሪዎቹ በ3 ነጥብ ርቆ 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።