​ወሳኙን ጨዋታ የሚያደርገው የብሔራዊ ቡድኑ አሠላለፍ ታውቋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከጫፍ የደረሰው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ ጋናን ሲገጥም የሚጠቀመው አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።

በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም በተደረጉት የማጣሪያ ጨዋታዎች የሩዋንዳ፣ ቦትሱዋና እና ታንዛኒያ አቻውን በጠቅላላ የድምር ውጤት 18ለ3 የረታው ቡድኑ ለዋናው ውድድር የ180 ደቂቃዎች ፍልሚያ ብቻ የቀረው ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላም የመጀመሪያ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያከናውናል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሁን ይፋ ባደረገው መሠረት አሠልጣኝ ፍሬው የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከታንዛኒያ ጋር ሲጫወቱ ከተጠቀሙት የመጀመሪያ የተጫዋቾች ምርጫ ረድኤት አስረሳኸኝን ብቻ በአረጋሽ ካልሳ ተክተዋል። በማጣሪያ ውድድሩ የቡድኑ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነችው ረድኤት ከወሳኙ ጨዋታ በጉዳት ምክንያት እንዳልተካተተችም ታውቋል።

የቡድኑ አሰላለፍ የሚከተለው ነው

ግብ ጠባቂ

22 እየሩሳሌም ሎራቶ  


ተከላካዮች

5 ናርዶስ ጌትነት      

6 ብርቄ አማረ 

4 ቤተልሔም በቀለ 

20 ብዙዓየሁ ታደሰ        


አማካዮች
 

2 ኝቦኝ የን       

10 ገነት ኃይሉ

17 መሳይ ተመስገን   


አጥቂዎች

11 አረጋሽ ካልሳ

13 ቱሪስት ለማ                       

14 አርየት ኦዶንግ