ወልቂጤ ከአጥቂው ጋር ተለያይቷል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ባለፉት ዓመታት ለወልቂጤ ከተማ ግልጋሎት ሲሰጥ የቆየው አጥቂ ዛሬ በስምምነት መለያየቱ እርግጥ ሆኗል።

አሰልጣኝ ተመስገና ዳና በሚፈልጉት መንገድ ቡድኑን ለማጠናከር በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ሲታወቅ የተፈለገውን ያህል አገልግሎት አልሰጡም ተብሎ ከሚታመኑ ተጫዋቾች ጋር በስምምነት መለያየት ጀምረዋል። አህመድ ሁሴንም ከክለቡ ጋር የተለያየ ተጫዋች ሆኗል።

የቀድሞው የቡታጅራ ከተማ አጥቂ ወደ ሠራተኞቹ ካመራ በኋላ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደረገ ሲሆን ቀሪ የስድስት ወር ኮንትራት ቢኖረውም ከወልቂጤ ከተማ ጋር ዛሬ በስምምነት መለያየቱ እርግጥ ሆኗል።

አህመድ በቅርቡ ወደ ሌላ የፕሪምየር ሊግ ክለብ ለማምራት ጫፍ ስለመድረሱም ለማወቅ ችለናል።