የዋልያዎቹ አሠልጣኝ ለአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

መጋቢት 16 ከኮሞሮስ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፏል።

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ መከናወኛ ወቅት የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ እንደነበር ይታወቃል። ከአስር ቀናት በኋላም ከኮሞሮስ አቻው ጋር ፍልሚያውን ከሜዳው ውጪ ያከናውናል። ለዚህ ጨዋታ ይረዳ ዘንድ ከሰሞኑን አሜሪካ የከረሙት የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ እና ረዳቶቻቸው 30 ተጫዋቾችን እንደጠሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

በጥሪው ላይ የአዲስ አበባው የግብ ዘብ ዳንኤል ተሾመ እና የመስመር አጥቂው ፍፁም ጥላሁን፣ የፋሲል ከነማው የመስመር ተከላካይ ዓለምብርሃን ይግዛው፣ የአዳማ ከተማው ተከላካይ ሚሊዮን ሰለሞን፣ የወልቂጤ ከተማው አማካይ አብዱልለሪም ወርቁ፣ የሀዋሳ ከተማው አማካይ ወንድማገኝ ኃይሉ፣ የሲዳማ ቡናው አጥቂ ይገዙ ቦጋለ፣ የመከላከያው የአጥቂ አማካይ ቢኒያም በላይ እንዲሁም የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ አጥቂ አቤል ያለው እና አማካይ በረከት ወልዴ ከአፍሪካ ዋንጫው ስብስብ በአዲስ መልክ ጥሪ የደረሳቸው ተጫዋቾች ናቸው።

ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረገው የተጫዋቾች ዝርዝር ከስር ተያይዟል 👇

ተጫዋቾቹም ከነገ በስትያ በመሰባሰብ ልምምዳቸውን እንደሚጀምሩ ተመላክቷል።