ሰበታ ከተማ ከአማካዩ ጋር ተለያይቷል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ለሁለተኛው ዙር የሊጉ ጨዋታዎች ዝግጅት ያልጀመረው ሰበታ ከተማ ከአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙር ደካማ ጊዜ በማሳለፍ በግርጌ ላይ የተቀመጠው ሰበታ ከተማ አስቀድሞ ከጂኒያንስ ናንጄቤ ፣ ፍፁም ተፈሪ እና መሀመድ አበራ ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ መስከረም ወር ላይ ክለቡን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሎ ከነበረው አማካዩ አክሊሉ ዋለልኝ ጋር በጋራ ስምምነት ተለያይቷል፡፡ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ጅማ አባጅፋር፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ ተጫዋች በያዝነው ዓመት ከሰበታ ጋር ቆይታን ለማድረግ ፊርማውን አኑሮ የነበረ ቢሆንም በአንድ ጨዋታ ላይ ብቻ ግልጋሎት ከሰጠ በኋላ በጋራ ስምምነት ተለያይቷል፡፡

በተያያዘ ዜና ከክፍያ አፈፃፀም እና ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተገናኘ የክለቡ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች በረከት ሳሙኤል እና የመስመር አጥቂው ሳሙኤል ሳሊሶ የመልቀቂያ ደብዳቤን ለክለቡ ማስገባታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡ክለቡ ለሁለተኛው ዙር የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች በተጫዋቾቹ የደመወዝ ጥያቄ መነሻነት እስከ አሁን ወደ ዝግጅት እንዳልገባም ለማወቅ ችለናል፡፡