አዲስ አበባ ከተማ አጥቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ከሰሞኑን ከሁለት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት የተለያየው አዲስ አበባ ከተማ በዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ተጫዋቹን የግሉ አድርጓል።

በአሠልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ የሚመራው አዲስ አበባ ከተማ ሊጉ በቀጣይ የሚደረግበት አዳማ ከተማ ቀድሞ በመግባት ዝግጅቱን እያከናወነ ሲገኘ ከአማካዩ ጋብሬል አህመድ እና የመስመር ተጫዋቹ ያሬድ ሀሰን ጋር በስምምነት እንደተለያየ መዘገባችን ይታወሳል። በክፍት ቦታዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ሲጥር የነበረው ክለቡም ከሰበታ ከተማ ጋር የተለያየውን ተስፋ የተጣለበት አጥቂ መሐመድ አበራን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

መሐመድ ከመከላከያ ተስፋ ቡድን 2012 ላይ ካደገ በኋላ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ የዘንድሮ የውድድር ዓመት ከመጀመሩ በፊት ወደ ሰበታ ከተማ ዝውውር ፈፅሞ ነበር። ተጫዋቹ ከረጅም ጉዳት በኋላ ወደ ሜዳ ቢመለስም በ15 ሳምንታት የሊጉ ጉዞ ከ99 ደቂቃዎች በላይ ክለቡን ማገልገል ሳይችል ከቀናት በፊት በስምምነት ተለያይቶ ነበር። የወረቀት ስራዎች ባይጠናቀቁም ተጫዋቹ በአሁኑ ሰዓት ስብስቡን በመቀላቀል አዳማ ላይ ልምምዱን እየሰራ እንደሚገኝ አውቀናል።