[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ስር የሚገኘው እና በዛሬው ዕለት ነቀምት ከተማን ላሸነፈው ኢትዮጵያ መድን የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
ከተመሠረተ ረጅም ዓመታትን ያስቅጠረው እና ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳትፎ የነበረው ኢትዮጵያ መድን በዘንድሮው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ስር በመደልደል ያለፉትን ጊዜያት ወደ ሊጉ ለማደግ ከጫፍ እየደረሰ ሲመለስ የነበረበትን ወቅት እውን ለማድረግ በዘንድሮው የ2014 የከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ የተሻለ ጉዞን እያደረገ ይገኛል፡፡ መርሐግብር ሊጠናቀቅ ሦስት ጨዋታዎች የሚቀሩት ሲሆን በዛሬው ዕለት ብርቱ ፉክክርን በምድቡ እያደረገ ከሚገኘው ነቀምት ከተማ ጋር ጨዋታውን ከውኖ 2-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በሁለት ነጥብ ልዩነት መምራት ጀምሯል፡፡
የዛሬውን ድል ተከትሎ የክለቡ አመራሮች በተገኙበት ክለቡ በሀዋሳ ክፍለ ሰላም ሆቴል ተገኝቶ የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማትን ያበረከተ ሲሆን በቀጣይ ለክለቡ አባላት የፕሪምየር ሊጉን የተሳትፎ ትኬት የሚቆርጡ ከሆነ ዳጎስ ያለ ሽልማት ስለመዘጋጀቱ በምሽቱ በተደረገው ስነ ሥርአት ላይ ከተጠቁሟል፡፡
አቶ ነፃነት ለሜሳ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና አስፈፃሚ እና የክለቡ የበላይ ጠባቂ “ቃል በገባችሁት መሠረት ቃላቸችሁን ጠብችኋል የዛሬው ጨዋታ ከማሸነፍ በላይ ነው፡፡ በዲሲፕሊን እየታነፃችሁ ውጤታማ እየሆነረችሁ ነው፡፡ ይህም ሊቀጥል ይገባል ከአሁን በኋላ ማሰብ የሚገባን እንዴት ተጠናክረን ለፕሪሚየር ሊጉ መዘጋጀት አለብን የሙለውን ነው።” በማለት የተናገሩ ሲሆን ስላስደሰታችሁን ደስ ብሎናል በማለትም ጭምር ሀሳባቸውን ለስፖርተኞቹ ገልጸዋል፡፡
በመቀጠል አቶ መንግሥቱ ማሩ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ምክትል ሥራ አስፈፃሚ እና የስፖርት ክለቡ ቦርድ አባል በበኩላቸው “ማሸነፍ ብቻ አይደለም ፤ በጣም ደስ ብሎናል። ይሄ ድል ከቀጠለ እኛ ሁሌም ከጎናችሁ ነን” ሲሉ በዋናነት ሀሳባቸውን አስቀምጠዋል፡፡ በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የሀዋሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል መኮንን ጨምሮ ፣ የክለቡ ስራ አስኪያጅ ኢንስትራክተር ይግዛው ቡዙአየው አሰልጣኝ ፣ በፀሎት ልዑልሰገድ እና ረዳቶቻቸው እንዲሁም የክለቡ ተጫዋቾች በየተራ የተሰማቸውን ስሜት የተናገሩ ሲሆን ድጋፉ መቀጠል እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡