[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
የጣና ሞገዶቹ በዝውውሩ የመጀመሪያ ተጫዋች የግላቸው ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ እየተመራ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ በሁለተኛው ዙር የሊጉ ውድድር በመጀመሪያው ዙር ላይ የገጠመውን ጉድለት ለመድፈን እና ተጠናክሮ ለመቅረብ ይረዳው ዘንድ ሁለገቡን ተጫዋች ሄኖክ ኢሳይያስን ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል ስምምነት ላይ ደርሷል።
የቀድሞው የደደቢት፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ወላይታ ድቻ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ከ2012 አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ ለድሬዳዋ ከተማ በአማካይ ተከላካይ እና በመስመር ተከላካይነት እየተጫወተ የነበረው ሄኖክ ከምስራቁ ክለቡ ጋር ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ባህርዳር ከተማን ምርጫው አድርጓል፡፡ ተጫዋቹ በአሁኑ ሰአት ከክለቡ ጋር የሚገኝ ሲሆን አመሻሹን የጣና ሞገደኞቹን በይፋ የሚቀላቀልም ይሆናል፡፡