በአምሐ ተስፋዬ
በአስረኛው ሳምንት በድሬዳዋ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ጨዋታውን ያከናወነው ወልቂጤ ከተማ የተጫዋች ተገቢነት ክስ መስርቷል።
የ2014 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር አስረኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ ማረፍ ያለበት ተጫዎች ተጠቅሞል የሚል ጭብጥ አለው። የወልቂጤ ከተማ ክስ በባለፏት ዘጠኝ ሳምንት አምስት ቢጫ የተመለከተ ተጨዋች አለ በማለት ክስ ያስመዘገቡት ወልቂጤዎች ለሀድያ ሆሳዕና ግብ ያስቆጠረው ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን ከኢትዮጽያ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ 90+3 የቢጫ ካርድ ማየቱን ተከትሎ በዘጠኝ ሳምንት ውስጥ በአጠቃላይ ያተመለከተው ቢጫ ካርድ አምስት መድረሱን ተመልክቶ ሊግ ካምፖኒው የላከው ኩሚኒኪ አባሪ በማድረግ አቅርበዋል።ተጫዋቹ መግባቱ ተገቢ አይደለም በማለት ክስ መስርተዋል። በዚህም መሠረት ተገቢው ወልቂጤ ከተማ ፎርፊ ይገባኛል የሚል ጥያቄ አቅርበዋል።
የሊግ ካምፓኒው የውድድር እና ስነ ሥርዓት ኮሚቴ የቀረበውን ክስ ጥያቄ ከመረመረ በኃላ በቅርቡ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።