አዲስ አበባ ከተማ ተጫዋች አስፈርሟል።

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ለውድድር ዘመኑ አጋማሽ እራሱን እያጠናከረ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርሟል።

አሰልጣኝ ደምሰው በክፍት ቦታዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም የሚያደርጉት ጥረት ቀጥሎ ባሳለፍነው ሳምንት መሐመድ አበራን ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸው ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በቅርቡ ኮንትራቱ ከአዳማ ከተማ ጋር የተጠናቀቀውን አማካይ ኤልያስ ማሞን ለአንድ ዓመት ማስፈረማቸው ታውቋል። የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ጅማ አባ ጅፋር አዳማ ከተማ እና ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተሰልፎ መጫወት የቻለው ኤልያስ ማሞ ካለው ልምድ አንፃር ለቡድኑ ጥሩ ግልጋሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በቀሩት የዝውውር ጊዜያት አዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ