የሰበታው ተጫዋች በክለቡ ላይ ያለውን ቅሬታ ለፌዴሬሽኑ አሳውቋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በ2013 የውድድር ዘመን ሰበታ ከተማን የተቀላቀለው ዱሬሳ ሹቢሳ በክለቡ ላይ ተፈፃሚ ያልሆኑልኝ ጉዳዮች አሉ በማለት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በደብዳቤ ቅሬታውን ገልጿል፡፡

ለቤቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን ላይ በብዙ ተግዳሮቶች እያለፈ የሚገኘው ሰበታ ከተማ ለሁለተኛው ዙር የሊጉ ጨዋታዎች እስከ አሁንም ወደ ልምምድ አለመግባቱ የሚታወስ ሲሆን የክለቡ ተጫዋቾችም ክለቡ የደመወዝ አፈፃፀምን ተግባራዊ አላደረገልንም በማለት የመልቀቂያ ደብዳቤን ማስገባት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ደግሞ የቀድሞው የአዳማ ከተማ እና አርሲ ነገሌ የመስመር አጥቂ ዱሬሳ ሹቢሳ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቤቱታውን በደብዳቤ ገልፆ አስገብቷል፡፡

ተጫዋቹ በደብዳቤው እንዳለው ከሆነ ”ክለቡን ከ2013 ጀምሬ በታማኝነት እያገለገልኩ እገኛለሁ። ነገር ግን ክለቡ በውላችን መሠረት ደመወዝ እና ጥቅማጥቅሜ አልፈፀመልኝም። በተደጋጋሚ ብጠይቅም የአራት ወር ደመወዜ ምላሽ አልተሰጠውም። የቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆኔ ክለቡ መልስ እንዲሰጠኝ ” በማለት ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤውን አስገብቷል፡፡