መከላከያ ከተስፈኛው ተጫዋች ጋር ተለያይቷል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው መከላከያ ከእድሜ እርከን ቡድኖቹ ጀምሮ ግልጋሎት ከሰጠው ተጫዋች ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ጉልህ ስም ካላቸው ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው መከላለያ በታችኛው የሊግ እርከን ሁለት ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ ባለንበት የውድድር ዓመት አድጎ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ይታወቃል። ክለቡ በመጀመሪያው ዙር ውድድር ክፍተት ባሳየባቸው ቦታዎች ግዢዎችን እያደረገ ሲገኝ ከአንድ ተጫዋች ጋር መለያየቱንም ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ቡድኑን ቀሪ የግማሽ ዓመት ውል እየቀረው የተለያየው ተጫዋች አቤል ነጋሽ ነው። ከ2008 ጀምሮ ጦሩን ከ17 ዓመት በታች ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ሲያገለግል የነበረው አቤል በዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ 377 ደቂቃዎችን ተጫውቶ አንድ ግብ በስሙ ማስመዝገቡ ይታወቃል። ከሦስት ዓመታት በፊት በዩጋንዳ አስተናጋጅነት በተደረገው ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ውድድር ላይም ኢትዮጵያን መወከሉ ይታወሳል።

ያጋሩ