[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ተጫዋች በማስወጣት እና በማስገባት የተጠመደው መከላከያ ከሦስት ተጫዋቾች ጋር መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ለሁለተኛው ዙር ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአዳዲስ ተጫዋቾች ስብስቡን እያጠናከረ የሚገኘው መከላከያ በተቃራኒው ከነባር ተጫዋቾቹ ጋርም እየተለያየ ይገኛል። ከዚህ አስቀድሞ ከኦኩቱ ኢማኑኤል እና አቤል ነጋሽ ጋር የተለያየው ክለቡ ዛሬ ደግሞ ከሌሎች ሦስት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ፍቺ ፈፅሟል።
ክለቡን የለቀቀው የመጀመሪያው ተጫዋች አለምአንተ ካሳ ነው። የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች የነበረው አለምአንተ በመጀመሪያው ዙር በሦስት ጨዋታዎች ላይ ብቻ በመሳተፍ በአጠቃላይ 184 ደቂቃዎችን ለጦሩ ግልጋሎት ሰጥቶ ነበር። ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ ገዛኸኝ ባልጉዳ ነው። አዲስ አበባን ከከፍተኛ ሊግ አሳድጎ ወደ ሌላኛው አዳጊ ክለብ ክረምት ላይ ተቀላቅሎ የነበረው አጥቂ ከ79 ደቂቃዎች በላይ የጨዋታ ዕድል ሳያገኝ መቅረቱ አይዘነጋም።
ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ ከክለቡ ጋር የተለያየው በመጀመሪያው ዙር ውድድር ከ44 ደቂቃዎች በላይ ግልጋሎት ያልሰጠው አኩዌር ቻም ነው። ሦስቱም ተጫዋቾች ቀሪ የግማሽ ዓመት ውል ከክለባቸው ጋር ቢቀራቸውም በስምምነት ተለያይተዋል።