በህይወት ላለፈው የቀድሞ ተጫዋች ቤተሰብ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ዩናይትድ ቤቭሬጅስ በተለያዩ ክለቦች እና የዕድሜ እርከን ብሔራዊ ቡድኖች ግልጋሎት ለሰጠው ሞገስ ታደሠ ቤተሰብ የ100 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ተገኝቶ የፈረሰኞቹን ዋናውን ቡድን በማገልገል የክለብ ህይወቱን ጀምሮ የነበረው ሞገስ ታደሠ በመቀጠል ወደ ሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ወልድያ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማቅናት ተጫውቶ እንዳሳለፈ ይታወቃል። በተለያዩ ዕእድሜ እርከን ቡድኖች ሀገሩን ያገለገለው የመስመር ተጫዋቹ አዳማ እያለ የመኪና አደጋ አጋጥሞት እጁ ላይ ጉዳት አስተናግዶ እንደነበር አይዘነጋም። በድንገተኛ አደጋ የተከሰተው ይህ ጉዳት ህመሙን አባብሶበት የነርቭ ችግር በመሆን ግማሽ ሰውነቱን ፓራላይዝ በማድረግ ለከፋ ህመም ከዳረገው በኋላ የካቲት 5 2012 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ከደቂቃዎች በፊት ከአዳማ ከተማ ጋር የ5 ዓመታት አጋርነት ስምምነት የፈፀመው ዩናይትድ ቤቭሬጅስ በዋሊን ቢራ ምርቱ ለክለቡ ግልጋሎት የሰጠው ሞገስን በማሰብ ለቤተሰቡ የ100 ሺ ብር ድጋፍ አበርክቷል። ይህንን ድጋፍም በአሁኑ ሰዓት በፅዳት ሥራ ላይ የተሰማሩት የሞገስ ወላጅ እናት ወ/ሮ ሠርካለም 7 ዓመቱ ላይ የሚገኘውን የሞገስ ልጅ ማሳደጊያ እንዲሆናቸው ከዩናይትድ ቤቭሬጅስት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ ወሬሳ እና የዩናይትድ ቤቨሬጅ ሴልስ እና ዲስትሪቢውሽን ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም ትዕዛዙ የገንዘብ ድጋፉን ተቀብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ወ/ሮ ሠርካለም ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪም በሚችሉት የሥራ ዘርፍ በተቋሙ እንዲሰሩ ዕድል መመቻቸቱም ተገልጿል።