[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ላለፉት አስር ቀናት በጁፒተር ሆቴል ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ዛሬ ምሽቱን በተደረገ ሥነ ስርዓት ተቋጭቷል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና ዋና ፃሀፊው ባህሩ ጥላሁን ከፍተውት በአቶ ባህሩ ጥላሁን መቋጫ ያገኘው ሥልጠና ላለፉት አስር ቀናት የተከናወነ ነበር። የካፍ እና የፊፋ ዳኞች ኢንስትራክተር በሆኑት ሞሪሺየሳዊው ሚስተር ሊም እና በግብፃዊው የካፍ የዳኞች የአይቲ ባለሙያ ራሚ ጋማል አማካይነት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ሁለት ዓይነት መልክ የነበረው ሲሆን በመጀመሪያው አምስት ቀናቶች ውስጥ ለጨዋታ ታዛቢዎች ሲሰጥ ቆይቶ በቀጣይ ለአምስት ቀናት ለዳኞች በሜዳ እና በክፍል ውስጥ ሲሰጥ ቆይቷል። ስልጠናው 22 የጨዋታ ታዛቢዎች እና 60 ዳኞች በሁለቱም ፆታዎች የተካተቱበትም ነበር።
የሥልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምሽቱን በጁፒተር ሆቴል ባዘጋጀው የመዝጊያ መርሐ ግብር ላይ ለአሰልጣኞች ሽልማት ሲሰጥ ሰልጣኞች ደግሞ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል። በሽልማት እና ምስጋናው ላይ ፌዴሬሽኑ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ ፣ ለጎፈሪ ትጥቅ አቅራቢ ድርጅት ፣ ለኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ እና ለብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ምስጋና አቅርቧል።