የብሔራዊ ቡድኑ አሰላለፍ ታውቋል

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጋናን የሚገጥው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ይፋ ተደርጓል።

በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚደረገው የዓለም የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ ማጣሪያ እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ 12:00 ላይ ከጋና አቻው ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል። ከሁለት ሳምንት በፊት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም 3-0 የተረታው ቡድኑ ውጤቱን ለመቀልበስ በሚያልምበት የዛሬው ጨዋታ ከሽንፈቱ ሁለት የአሰላለፍ ለውጥ አድርጓል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ ባደረገው አሰላለፍ መሰረት አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ቤተልሄም በቀለ እና አርያት ኦዶንግን አሳርፈው በምትካቸው ነፃነት ፀጋዬ እና ማዕድን ሳህሉን በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ አካተዋል።

የቡድኑ ሙሉ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ግብ ጠባቂ

22 እየሩስዓሌም ሎራቶ

ተከላካዮች

5 ናርዶስ ጌትነት (አ)
6 ብርቄ አማረ
12 ነፃነት ፀጋዬ
20 ብዙአየሁ ታደሰ

አማካዮች

2 ኝቦኝ የን
10 ገነት ኃይሉ
21 መዕድን ሳህሉ

አጥቂዎች

11 አረጋሽ ካልሳ
13 ቱሪስት ለማ
17 መሳይ ተመስገን

ያጋሩ