የምድብ ሐ ወሳኝ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት እንዲደረጉ ተወሰነ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ እና ወደ አንደኛ ሊግ ላለመውረድ ብርቱ ትግል የሚኖራቸው አራት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት እንዲደረጉ ተወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ ወሳኝ ጨዋታዎች በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ከተደረጉ በኋላ ወደ 2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚያድገውን አንድ ቡድን የሚለይ ሲሆን ወደ አንደኛ ሊግ የሚወርዱ ሁለት ቡድኖችም የሚታወቁ ይሆናል፡፡ በዛሬው ዕለት ክለቦች ባደረጉት ስብሰባ ለማደግም ሆነ ላለመውረድ የሚደረጉ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት መሆን አለባቸው በሚል በሙሉ ድምፅ ተስማምተዋል። ነቀምት ከተማ በአርቴፊሻል ሜዳ ላይ የማደርገው ጨዋታ ይለወጥልኝ ቢልም በአብላጫ ድምፅ በመፅደቁ ጥያቄው ውድቅ መደረጉን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡በዚህም መሠረት የፊታችን ዓርብ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ የአንድ ነጥብ ልዩነት ያላቸው ክለቦች በተመሳሳይ ሰዓት ይጫወታሉ፡፡ ይህንን ተከትሎም 9፡00 ነቀምት ከተማ ከየካ ክፍለ ከተማ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ላይ ሲጫወቱ ኢትዮጵያ መድን ከ ደቡብ ፓሊስ ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

በዛኑ ቀን ዓርብ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ላይ ወደ አንደኛ ሊጉ የሚወርዱ ክለቦች የሚለዩ ጨዋታዎችም ይደረጋሉ፡፡ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ላይ ፌዴራል ፖሊስ ከ ወላይታ ሶዶ ከተማ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ሜዳ ላይ ደግሞ በእኩል ሰዓት ሀምበሪቾ ዱራሜ ከ ጅማ አባቡና ይጫወታሉ፡፡ ከዓርብ ቀደም ብሎ መርሐ-ግብር ለማሟላት ሀሙስ 3፡00 ሰዓት ላይ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከ አቃቂ ቃሊቲ ይገናኛሉ፡፡