የከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ ወሳኝ ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት ይደረጋሉ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የመጨረሻ ሳምንት የፕሪምየር ሊግ አላፊ ቡድንን የሚለዩት ሁለት ጨዋታዎች ቦታ እና ሰዓት ታውቋል።

የ2014 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሊጠናቀቅ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ብቻ ይቀራሉ፡፡ በባቱ ከተማ እየተደረገ በሚገኘው የምድብ ለ መርሐግብር ወደ 2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሻገረውን አንድ ቡድን ለይቶ እስከ አሁን አላሳወቀም፡፡ በዚህም መነሻነት በመጨረሻው ሳምንት ወደ ሊጉ የሚያድገውን ቡድን ለመለየት የፊታችን ዓርብ ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት በሁለት ሜዳዎች እንዲደረጉ ማምሻውን የምድቡ ክለቦች በባቱ ከተማ ባደረጉት ስብሰባ ተለይቶ ታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት ዓርብ 4፡00 ሰዓት ሲል ሊጉን እየመራ የሚገኘው ለገጣፎ ለገዳዲ እና ሰንዳፋ በኬ በባቱ ስታዲየም ሲጫወቱ ተከታዩ ቤንች ማጂ ቡና ከኮልፌ ቀራኒዮ በተመሳሳይ ሰዓት በሼር ሜዳ እንዲጫወቱ ሰዓት ተቆርጦላቸዋል፡፡ ሐሙስ ዕለት ደግሞ 4፡00 ሲል ስልጤ ወራቤ ከከንባታ ሺንሺቾ ፣ 8፡00 ላይ ቡታጅራ ከተማ ከ ቂርቆስ ክፍለከተማ ፣ 10፡00 ላይ ካፋ ቡና ከ ቡራዩ ከተማ ለመርሐ ግብር ማሟያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ያጋሩ