የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 1-1 ፋሲል ከነማ

በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀው የምሽቱ ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከተዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ሙሉጌታ ምህረት – ሀዲያ ሆሳዕና

መሀል ሜዳ ላይ ስለነበራቸው የቁጥር ብልጫ

“ይህን የጨዋታ መንገድ የመረጥነው ከተጋጣሚያችን ጥንካሬ አንፃር ነው። እነሱ ጥራት ያላቸው እንዲሁም ብዙ አብረው የቆዩ ናቸው። እኛ ግን ዘንድሮ የተሰባሰብን ነን። ከዚህ አንፃር ይዘን የገባነው ዕቅድ ከሞላ ጎደል ጥሩ ነበር።

ስለቡድኑ የማጥቃት ሂደት እና አለመረጋጋት

“ጥሩ አጋጣሚዎችን መፍጠር ብንችልም የተሻለሉ አማራጮችን እየነበሩ እነሱን በችኮላ መጠቀም አለመቻላችን አይተናል። ጎሎችን ብናስቆጥር ግን ይበልጥ መረጋጋት እንችል ነበር። መረጋጋት ብንችል የተሻለ ውጤታማ መሆን በቻልን ነበር። ነገርግን ግብ አግኝተንም ስንቻኮል ነበር።”

ስዩም ከበደ – ፋሲል ከነማ

ስለመሀል ሜዳቸው

“በመጀመሪያው አቀራረባችን ላይ በሁለት አጥቂ እንደመጫወታችን ለኦኪኪ የሰጠነው ኃላፊነት ከሙጂብ ጋር እንዲቆም ሳይሆን ይበልጥ ወደ ኋላ ተስቦ እንዲጫወት ነበር። ነገርግን ይህን ሲያደርግ አልተመለከተንም ፤ ሁለቱም ፊት ላይ ተነጥለው ይቀሩ ነበር። ለዚህም ሀዲያ በአጋማሹ መሀል ላይ የተሻሉ እንዲሆኑ አስችሏል። በሁለተኛው አጋማሽ ግን መሻሻሎችን አድርገን ማስቆጠር ችለን ነበር። ነገርግን የቆመ ኳስ ላይ በነበረን የትኩረት ማጣት አቻ ሆነናል።

ስለ ሙጂብ ቃሲም እንቅስቃሴ

“በሁለት መልኩ መመልከት ይገባል። አንደኛ እሱም ከጨዋታ ርቆ መቆየቱ በተወሰነ መልኩ በሂደት እየተስተካከለ የሚመጣ ነው። ሌላው አማካዮቻችን የነበራቸው ጥምረት የመጨረሻ ኳስ በማቀበል ሆነ በመስመሮች በኩል የነበረን ነገር ጥሩ አለመሆኑም ተፅዕኖ ፈጥሮበታል።

ከመሪው ጋር ስለተፈጠረው ልዩነት

“ከዚህ በፊትም እንደምለው ለምሳሌ በ2011 ፋሲል በ10 ነጥብ ልዩነት ቢመራም በመጨረሻ የነበረው ትንንቅ ይታወሳል። ብቻ ዋናው ነገር እኛ ጥንካሬ እና ወደ ውጤት መምጣት ነው ፤ እኛ ግን እስከመጨረሻው ትግላችን አይቆምም።”