ወልቂጤ ከተማ አማካይ አስፈርሟል

ለሁለተኛው ዙር ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት ባሉበት ክፍት ቦታዎች ላይ አዳዲስ ተጫዋቾችን እያመጣ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ አማካይ አስፈርሟል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና መሪነት ከአዳማ ከተማ ጋር 1ለ1 በመለያየት ሁለተኛውን ዙር የጀመረው አዳማ ከተማ ኡጋንዳዊውን ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ እና ሁለገቡ ቤዛ መድህን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ አማካዩ አክሊሉ ዋለልኝን ሦስተኛ ፈራሚው አድርጓል፡፡

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ጅማ አባጅፋር ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ ተጫዋች በያዝነው የውድድር አመት ከሰበታ ከተማ ጋር ቆይታን ለማድረግ የሁለት አመት ፊርማውን አኑሮ የነበረ ቢሆንም ከክለቡ ጋር ቀሪ ኮንትራት እየቀረው ከወራት በፊት በመለያየት መዳረሻውን ወልቂጤ በማድረግ ከቡድኑ ጋር ተቀላቅሏል፡፡

ያጋሩ