ከሲዳማ ጋር ውል ያፈረሰው አዲስ ፈራሚ ወደ ወልቂጤ አምርቷል

ወልቂጤ ከተማ ከቀናቶች በፊት ለሲዳማ ፈርሞ በስምምነት የተለያየውን አማካይ አስፈረመ፡፡

ወልቂጤ ከተማ ሮበርት ኦዶንካራ ፣ ቤዛ መድህን እና ከአክሊሉ ዋለልኝ በመቀጠል አራተኛ ተጫዋቹን በእጁ አስገብቷል፡፡በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ያሰበው ክለቡ ከሳምንት በፊት ለሲዳማ ቡና ፈርሞ የነበረውን የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜግነት ያለውን አማካይ በስምምነት በመለያየቱ ወልቂጤ ከተማ የግሉ አድርጎታል፡፡

የተከላካይ አማካይ እንዲሁም በአማካይ ስፍራ ላይም ጭምር መጫወት የሚችለው ኤዲ ኢሞሞ ኒጎዬ ነው፡፡ ሰራተኞቹን የተቀላቀለው ተጫዋቹ ለትውልድ ሀገሩ ክለቦች ሻርክስ ዢ እና ኤ ኤስ ካቫሻ ለተባሉ ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው እና በመቀጠል ለቱኒዚያው ዩ ኤስ ሞናስትሪ ከዛም ለግብፁ ሶሞሀ እንዲሁም ያለፉትን አመታት ወደ ሀገሩ ተመልሶ ለኤ ኤስ ቪታ ክለብ ተጫውቶ የነበረው ይህ የውጪ ዜጋ ለሲዳማ ቡና ለአንድ አመት በቅርቡ መፈረም ችሎ የነበረ ቢሆንም በስምምነት ትላንት ተለያይቶ ወደ ሌላኛው የሀገራችን ክለብ ወልቂጤ አምርቷል፡፡

ያጋሩ