በትናትናው ዕለት ከዋናው አሰልጣኙ ጋር የተለያየው ፋሲል ከነማ በቀጣይ ቡድኑን የሚመሩ አሰልጣኞች ታውቀዋል።
በወቅታዊ ውጤት ማጣት ምክንያት ከአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ጋር ትናንት ማምሻውን በስምምነት ለመለያየት የወሰኑት የፋሲል ከነማ አመራሮች በቀጣይ ቡድኑን እስከ ሰኔ 30 ድረስ በዋና እና በምክትል አሰልጣኝነት የሚመሩትን ግለሰቦች አሳውቀዋል። በዚህም መሠረት ክለቡ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ያገለገሉት ኃይሉ ነጋሽ (ቲጋና) ወደ ዋና አሰልጣኝነት ከፍ አድርጎ ሲሾም እንዲሁ በሁለተኛ ምክትልነት ኃላፊነት የነበራቸው ሙልቀን አቡሃይን በዛው የሥራ ድርሻቸው እንዲቀጥሉ ወስኗል።
ዘለግ ላለ ሰዓት በትናትናው ምሽት ከተጫዋቾቹ ጋር ስብሰባ የተቀመጠው የክለቡ ቦርድ አሉ በሚባሉ ክፍተቶች ዙርያ ሰፊ ውይይት ማድረጉ ሲታወቅ ሌሎች ውሳኔዎችን በቀጣይ ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።