የአሰልጣኞች አስተያየት | ሲዳማ ቡና 3-1 ሀዋሳ ከተማ

ከምሽቱ የደርቢ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ስለ ጨዋታው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ

ስለጨዋታው

“ጎሉ የገባበት መንገድ ትንሽ አለመረጋጋቶች ነበሩ፡፡ ጨወታው ተመጣጣኝ ነው ፤ ጥሩ ፉክክር የታየበት ነው፡፡ ብልጫውን ለመውሰድ በተለይ ጎሉን ካገባን በኋላ ጥረት አድርገናል። በሰራነው ስህተት ሁለተኛው ኳስ መግባቱ ትንሽ መውረድ ቢኖርም ግን በእንቅስቃሴው ተመልሰን ወደ ማጥቃቱ ገብተን ነበር፡፡በተደጋጋሚ ወደ ጎል እየቀረብን ነበር መጨረሻ ላይ ግን ኮርና ኳስ የጀመርነው ኳስ ነው ምክንያቱም ለመልሶ ማጥቃት እነሱም ዝግጁ ነበሩ። እና ጎዶሎም ስለሆኑ ለመልሶ ማጥቃት ነው የሚዘጋጁት እና ዞሮ ዞሮ አንደኛው የሚቆመው ሰው ማርክ አላደረገውም የመጨረሻውን አጥቂ ከዛ በኋላ መጀመር አልነበረበትም ኮርናው ያው ተመሳሳይ ስህተት ነው፡፡ በእንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነበር ዞሮ ዞሮ በሰራናቸው ጥቃቅን ስህተቶች ተሸንፈን ወጥተናል ይሄ እግርኳስ ነው፡፡ ለቀጣይ ጨዋታ ማሰብ ነው፡፡

ወንድማገኝ ኃይሉ በቡድኑ ውስጥ አለመኖሩ በማጥቃት ላይ ስለፈጠረው ተፅዕኖ

“አዎ ምንም ጥያቄ የለውም። ይሄን ያህል የከፋ ክፍተት ባይኖርም የእሱ መኖር እዛ ጋር ቢያንስ በተለይ ዛሬ የምናገኛቸውን አጋጣሚዎችን በሱ ድሪብል ማቋረጥ ስለሚቻል ፤ መጀመሪያም ያ እንደሚያጋጥም ግልፅ ነው፡፡ዞሮ ዞሮ ቡድኔ ያደረገው ነገርም ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል። ይሄን ያህል ክፍተት ባይኖርም ቢኖር የተሻለ ነው ምንም ጥያቄ የለውም። ግን ይሄን ያህል ቡድኑ ያደረገው እንቅስቃሴ ህዝቡም ተደስቶ ወጥቷል ብዬ አስባለሁ እና ጨዋታው በዚህ ማለቅ አልነበረበትም ቢያንስ እንደ እንቅስቃሴያችን። ግን ያው በሰራናቸው ስህተቶች ዋጋ ከፍለናል ፤ ታርመን እንመጣለን፡፡”

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ – ሲዳማ ቡና

ስለጨዋታው

“ጥሩ ነው እንግዲህ ዛሬ ተሳክቶልናል ማለት ይቻላል ባሰብነው መንገድ ሄዷል፡፡ እንደ አቀራረባችን ኳሱን ተቆጣጥሮ በቁጥጥር ስር አድርጎ በጋራ የማጥቃት በተለይ ደግሞ የመስመሩን ብቻ ሳይሆን መሀል ለመሀል የማጥቃት ዘዴ ይዘን መጥተናል። እሱን ለመጠቀም በተወሰነ መልኩ ችለናል ማለት ይቻላል እና በአጠቃላይ ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ ሦስት ነጥብ ያስፈልገን ስለነበረ አሳክተነዋል ጥሩ ነው፡፡

በጨዋታው ስለነበሩ ተደጋጋሚ ጥፋቶች

“ይሄ የደርቢ ስሜት አለ፡፡ የደርቢ ስሜት የሚፈጥረው ኃይል የተቀላቀለበት ጨዋታ እንደሚኖር የታወቀ ነው፡፡ በእኛ በኩል ያን ያህል ኃይል የተቀላቀለበትን ጨዋታ አልተጫወትንም። ነገር ግን ያው በእነሱ በኩል መጀመሪያም አጨዋወታቸው ኃይል የተቀላቀለበት ጨዋታ ሊጫወቱ እንደሚችሉ እናውቅ ነበር፡፡ በተወሰነ መልኩ በጣም ጥሩ ነው ተቆጣጥረውታል ማለት ይቻላል፡፡

በቀጣይ ስለሚያስቡት ነገር

“እንግዲህ ገና አሁን ወደ አዳማ ከመጣን ሦስተኛ ጨዋታዎችን ነው፡፡ የመጀመሪያ ጊዜ ነው ሦስት ነጥብ ስናገኝ አቻ ወጥተን ነበር እና ማጣት የማይገባን ነጥቦችን አጥተናል። ከዚህ ቀደም ያጣናቸውን ነጥቦች ከዚህ በኋላ ባሉ ጨዋታዎች ላይ እንዳይደገሙ ጥንቃቄ ያለውን ጨዋታ እየተጫወትን የሚቻለውን ወደ ፊት እየሄድን ለመጠጋት ጥረት እናደርጋለን።”