
ጅማ አባ ጅፋር ከሦስት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቷል
በወራጅ ቀጠናው የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር በስምምነት ከሦስት ተጫዋቾች ጋር መለያየቱ ታውቋል።
በአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው ጅማ አባጅፋር በዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ 18 ጨዋታዎችን አድርጎ 12 ነጥቦችን በመሰብሰብ 15ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ቡድኑ ቀድሞ ከሦስት ተጫዋቾች ጋር ከተለያየ በኋላ በቀሪ ጨዋታዎች በሊጉ ለመትረፍ በውሰት አራት ተጫዋቾችን ያመጣ ሲሆን በቋሚነት ደግሞ የግብ ዘቡ ሀሪሰን ሄሱን ለማስፈረም ቢስማማም እስካሁን የወረቀት ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው የተጫዋቹን ውል ማፀደቅ አልቻለም።
አሁን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ደግሞ ተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾች በስምምነት ከቡድኑ መለየታቸውን ይጠቁማል። የመጀመሪያው ተጫዋች ስብስቡን ከቅዱስ ጊዮርጊስ በውሰት ተቀላቅሎ የነበረው ትንሳኤ ያብጌታ ነው። ከ45 ደቂቃዎች በላይ በአባ ጅፋሩ ቤት ግልጋሎት ካልሰጠው ትንሳኤ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ከሀዋሳ ከተማ በውሰት የመጣው እና አንድ ጨዋታ የተጫወተው ብሩክ ሙሉጌታም እንደ ትንሳኤ ቡድኑን ተለያይቷል። ከሁለቱ በተጨማሪ ከከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሀላባ ከተማ በአንድ ዓመት ውል ፈርሞ አንድም ደቂቃ በሜዳ ያልተመለከትነው አብዱልሰመድ መሐመድም በስምምነት ክለቡን መልቀቁ ተመላክቷል።
ተዛማጅ ፅሁፎች
የአሰልጣኞች አስተያየት | ወልቂጤ ከተማ 3-0 ጅማ አባ ጅፋር
ከረፋዱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ተመስገን ዳና - ወልቂጤ ከተማ ስለጨዋታው "መውረዱን...
ሪፖርት | ወልቂጤ የሊጉ ቆይታውን ለማረጋገጥ ተቃርቧል
በ29ኛ የጨዋታ ሳምንት የመክፈቻ በነበረው መርሐ-ግብር አምበሉ ጌታነህ ከበደን መልሰው ያገኙት ወልቂጤ ከተማዎች ጅማ አባ ጅፋርን በመርታት ደረጃቸውን አሻሽለዋል። ወልቂጤ...
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የሊጉ መሪ ንግድ ባንክ እና ተከታዩ ኤሌክትሪክ ሲያሸንፉ ሀዋሳ እና መከላከያ ነጥብ ተጋርተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በአዳማ ሲከወኑ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ንግድ ባንክ በግብ ሲንበሸበሽ ተከታዩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ...
ቅድመ ዳሰሳ | የ29ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ሦስት ጨዋታዎች ቅድመ ምልከታ
የ29ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ሦስት ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ቃኝተናቸዋል። በዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ፉክክሩ እና ላለመውረድ ትንቅንቁ ቀጠሎ እስካለንበህ የ29ኛ...
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ቅጣት ተላለፈባቸው
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል። ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት ዕድሜ የቀረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...
አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹን ሸኝቷል
ከወረጅ ቀጠናው ለመውጣት እየጣረ የሚገኘው አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹን በዲሲፕሊን ምክንያት ከስብስቡ መቀነሱ ታውቋል። በ28ኛ ሳምንት ከመከላከያ ጋር ያለ ጎል...