የአሰልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 0-1 ፋሲል ከነማ

በፋሲል ከነማ የበላይነት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ኃይሉ ነጋሽ – ፋሲል ከነማ

ስለ ጨዋታው

“መቆራረጦች ቢኖሩም ኳሱን ለመያዝ ሞክረናል ይህን አሻሽለን ለመምጣት እንሞክራለን ነገርግን ውጤቱ አስፈላጊ ከመሆኑ አንፃር በጣም ደስተኞች ነን።”

በክፍት ጨዋታ ዕድሎችን ለመፍጠር ስለመቸገራቸው

“የአርባምንጮችም የመከላከል ሂደት ጠንካራ ነበር በአንፃሩ እኛም ወደ ማጥቂያው ሲሶ የምንደርስበት መንገድ ጥሩ አልነበረም እሱን ደግሞ ይበልጥ አሻሽለን እንመጣለን።”

ስለበዛብህ መለዮ ግብ አስቆጣሪነት

“በዛብህ አምናም ቢሆን በጣም ጥሩ ነበር ከመሀል እየተነሳ ግቦችን ማስቆጠር የሚችል ለጎል ቅርብ የሆነ ተጫዋች ነው ይህንን አቅሙን ከዚህ በላይ አሻሽሎ ይመጣል ብዬ አስባለሁ።”

ሁለትኛ ደረጃ ላይ ስለመቀመጣቸው

“አሁን እኛ የምናስበው ብቸኛ ነገር ከፊት ያሉትን ጨዋታዎች ከዛሬ ስህተት ተምረን ማሸነፍ እንችላለን ስለሚለው ጉዳይ ነው።”


መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ ከተማ

ስለጨዋታው

“ከገባብን በኃላ በዚያ መልኩ መጫወት አልነበረብንም በጥቅሉ በምንፈልገው ልክ አልሄደለንም ፤ ግብ ከተቆጠረብን በኃላ ያሳየነውን ነገር ሙሉ ጨዋታው ላይ ማሳየት ነበረብን።”

አፈግፍገው ስለመጫወታቸው

“ስንገባ የትኛውንም ጨዋታ አሸንፈን ለመውጣት ነው ፤ ነገርግን ባለ ጋራ ኳሱን ሲቆጣጠርብህ በተወሰነ መልኩ ከኳስ ጀርባ ስለምንሆን ያፈገፈግን ሊመስል ይችላል።

ከዘጠኝ በኃላ ስለመሸነፋቸው

“አንዳንዴ መውረድ ያጋጥማል በእግርኳስ አንዳንዴ ወጥ የሆኑ ነገሮች ላይኖሩ ይችላሉ ፤ ግን መጨረሻ ላይ የነበረን አይነት እንቅስቃሴ በሙሉ ዘጠና ደቂቃው ብናሳይ ጥሩ ነበር ብዬ አስባለሁ።”