የሁለተኛ ዙር የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ጊዜ እና ቦታ ታውቋል

በ13 ክለቦች መካከል እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድር የሚጀምርበት ቀን እና ቦታን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥር የሚከናወነው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ዘንድሮ ጅማሮውን በሀዋሳ አድርጎ በአሁኑ ሰዓት በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። በቀጣዩ ሳምንት የመጀመሪያ ቀናትም የመጀመሪያውን ዙር ውድድር የሚያገባድድ ይሆናል። የሊጉ የበላይ አካል የሆነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሁን እንዳስታወቀው ከሆነ ደግሞ የሁለተኛው ዙር ውድድር ከግንቦት 14 ጀምሮ በአዳማ ከተማ ይከናወናል።

ለክለቦቹ በተላከው ደብዳቤ መሠረት የመጀመሪያው ዙር ውድድር ሚያዚያ 25 ከተከባደደ በኋላ ከሚያዚያ 29 ጀምሮ እስከ ግንቦት 12 ድረስ የውድድር አጋማሽ የዝውውር መስኮት ክፍት እንደሚሆን ተጠቁሟል።