ከ22ኛ ሳምንት ጀምሮ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ማስተካከያ ተደርጓል

በባህር ዳር ከተማ ከ22ኛ እስከ 25ኛ ሳምንት ድረስ የሚደረጉት ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ማስተካከያ ሲደረግ በቀን ሦስት ጨዋታዎች እንዲከናወኑም መርሐ-ግብር ወቷል።

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በሀዋሳ ጅማሮውን በማድረግ በድሬዳዋ ዘልቆ በአሁኑ ሰዓት በአዳማ ከተማ እየተከናወነ ይገኛል። ያለንበት ሳምንት ከነገ በስትያ ከተገባደደ በኋላ ደግሞ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ባህር ዳር ላይ መደረግ ይጀምራሉ። ለአይቮሪኮስቱ የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ያሉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ታሳቢ በማድረግም የሊጉ የበላይ አካል አዲስ መርሐ-ግብር አውጥቷል።

በዚህም ከ22ኛ ሳምንት ጀምሮ እስከ 25ኛ ሳምንት ድረስ የሚደረጉ ጨዋታዎች ሁሉም በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ሲደረጉ በቀን ሦስት ጨዋታዎች 4፣ 7 እና 10 ሰዓት እንዲደረግ መወሰኑን አውቀናል።

የ22ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የሚከተለው ነው

ቅዳሜ ሚያዚያ 29

4:00 ጅማ አባ ጅፋር ከ አርባምንጭ ከተማ
7:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ
10:00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ መከላከያ

እሁድ ሚያዚያ 30

4:00 ሰበታ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
7:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ
10:00 ወላይታ ድቻ ከ ባህር ዳር ከተማ

ሰኞ ግንቦት 1

4:00 ሲዳማ ቡና ከ ፋሲል ከነማ
10:00 ወልቂጤ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ