የአሰልጣኞች አስተያየት | ድሬዳዋ ከተማ 2-0 ሰበታ ከተማ

ለድሬዳዋ ከተማ ትልቅ ዋጋ ያለውን ሦስት ነጥብ ካስገኘው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ሳምሶን አየለ – ድሬዳዋ ከተማ

ስለጨዋታው

“ያለንበት ቀጠና በጣም አስጨናቂ ነው ከዚህ ለመውጣት ያለን አማራጭ ያገኘነውን አጋጣሚ ተጠቅመን አሱን አስጠብቀን መውጣት ነው ከዚህ አንፃር ያሰብነውን አሳክተናል።”

የመጀመሪያውን ግብ ካስቆጠሩ በኋላ ስለነበረው ሂደት

“በስጋት ውስጥ ነበርን ዕቅዳችን በምንፈልገው ደረጃ ነው ለማለት ይከብዳል ነገርግን ከስጋት በመነጨ አቅማቸውን አውጥተው እየተጠቀሙ አይገኝም ይህም ደግሞ ከጫናው የመጣ ነው።”

በባህር ዳር ሰለሚኖራቸው እቅድ

“በርካታ ጨዋታዎች ከፊት ይቀራሉ ነገር ግን ድሉ ልጆቻችን ላይ ከፍተኛ መነቃቃት ይፈጥራል ይህም ለቀጣይ ትልቅ ጉልበት ይሆናል ከዚህም መነሻነት በመከላከሉ ሆነ በማጥቃቱ በተለይ ያሉብንን ከፍተቶች አሻሽለን እንቀርባለን።”

ብርሃኑ ደበሌ – ሰበታ ከተማ

ስለጨዋታው

“ጨዋታው እኔም ራሱ ግራ ነው የገባኝ የተዘጋጀንበትን ነገር ሜዳ ላይ አልተመለከትንም ነገር ግን ጨዋታው ለማሸነፍ ጥረት አድርገናል ግን አልተሳካም ቢሆንም ግን ተጋጣሚ ቡድንን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ።”

ቅያሬዎቹ ስለፈጠሩት ለውጥ

“በተቻለ መጠን አጥቅተን ግብ እንድናስቆጥር የሚረዳ አላማ ሰጥተን ነው ያስገባናቸው ሆኖም ግን ውጤታማ አላደረጉንም ፤ ወደ ጎል በተደጋጋሚ ብንደርስም የማስቆጠር ችግራችን አሁንም እንዳለ ነው።”

በሊጉ ስለመቆየት እድላቸው

“እጅግ ፈታኝ ነው ፤ እግር ኳስ ነው የሚሆነው ባይታወቅም ጠንክረን መቅረብ ይኖርብናል ለዚህም ስህተቶቻችን በደንብ ቀርፈን መቅረብ ይኖርብናል።”