አዲስ አበበ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

በዘንድሮ ዓመት ወደ ሊጉ ያደገው አዲስ አበበ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

በአሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር እየተመራ የሦስት ሳምንት የሊጉን ውድድር ጅማሮ ካደረገ በኋላ መለያየቱን ተከትሎ ምክትል አሰልጣኙን ደምሰው ፍቃዱን በጊዜያዊነት ክለቡ መሾሙ ይታወቃል።

አሰልጣኝ ደምሰውም እስከ ሃያ አንደኛው ሳምንት ድረስ ቡድኑን እየመሩ ቢቆዩም በዛሬው ዕለት ከክለቡ አመራሮች ጋር በመነጋጋገር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።

ነገ ጠዋት ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚያቀናው ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን በቅርቡ የሚያሳውቅ መሆኑን ሰምተናል።

ያጋሩ