ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታን ይመራሉ

ማፑቶ ላይ የሚደረገውን የሞዛምቢክ እና የሩዋንዳ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመሩታል፡፡

የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡ በዚህም ውድድር ላይ ሀገራት ተካፋይ ለመሆን በምድብ ተደልድለው የማጣሪያ ጨዋታዎችን ይከውናሉ፡፡ በምድብ – 12 ሴኔጋል ፣ ቤኒን ፣ ሞዛምቢክ እና ሩዋንዳ የሚገኙበት ሲሆን የምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ከአንድ ወር በኋላ ይካሄዳሉ፡፡

በዚህ ምድብ ማፑቶ ላይ ሚያዝያ 26 ምሽት 1፡00 ሰዓት ሲል በዚምፒቶ ስታዲየም ሞዛምቢክ ሩዋንዳን በሜዳዋ የምትገጥምበትን ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች እንዲመሩት ስለመመረጣቸው ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች፡፡

የፊታችን ቅዳሜ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የአል-ህሊን እና ኢ ኤስ ሴቲቭን ጨዋታ የሚመራው በዓምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ለዚህ ጨዋታ ሲመደብ ተመስገን ሳሙኤል እና ፋሲካ የኋላሸት በረዳትነት ቴዎድሮስ ምትኩ ደግሞ በአራተኛ ዳኝነት ጨዋታውን እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡