በድሬደዋ ከተማ አስተናጋጅነት ከነገ ጀምሮ የሚጀምረው የአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል።
በ2015 ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚያድጉ ስድስት ቡድኖችን ለመለየት በ18 ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የአንደኛ ሊግ የማጠቃልያ ውድድር ከሚያዚያ 29 ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ቀን ድረስ በድሬደዋ ከተማ አስተናጋጅነት በአራት ምድብ ተከፍሎ ይካሄዳል።
ዛሬ ረፋድ ላይ በድሬደዋ ወጣቶች ስፖርት ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የደንብ ውይይት ከክለብ ተወካዩች ጋር ከተደረገ በኋላ የምድብ ድልድሉ ይፋ ሆኗል።
በዚህም መሠረት
በምድብ ሀ
ሆለታ ከተማ
ጎፋ ባሬንቺ
ሐረር ከተማ
ሮቤ ከተማ
መከላከያ ቢ
ምድብ ለ
ሱሉልታ ከተማ
አንጋጫ ከተማ
ቡሌ ሆራ
ጂንካ ከተማ
ዱራሜ ከተማ
ምድብ ሐ
አረካ ከተማ
ቦዲቲ ከተማ
ዱከም ከተማ
አዲስ ከተማ ክ/ከተማ
ምድብ መ
አራዳ ክ/ከተማ
ድሬደዋ ፖሊስ
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ
ልደታ ክ/ከተማ
ውድድሩ ነገ በድሬደዋ ስታዲየም ሲጀምር
03:00 | ሆለታ ከተማ ከ ጎፋ ባሬንቺ
05:00 | ሐረር ከተማ ከ ሮቤ ከተማ
08:00 | ሱሉልታ ከተማ ከ አንጋጫ ከተማ
10:00 | ቡሌ ሆራ ከ ጂንካ ከተኛ