የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 2-1 አርባምንጭ ከተማ

ከቀናት ዕረፍት በኋላ ሊጉ በባህር ዳር ሲጀምር ጅማ አባ ጅፋር ድል ካደረገ በኋላ አሰልጣኞቹ አስተያየት ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ የሱፍ ዓሊ – ጅማ አባ ጅፋር

ስለተከታታይ ድላቸው

“ካለው ተነሳሽነት እና በሂደት ከምንሰራቸው ነገሮች አንፃር ጥሩ ነገር እንደሚመጣ ነበር አስበን ስንሰራ የነበረው። የልጆቹ ተነሳሽነት ደስ ይላል። ይሄንን ለማስቀጠል ነው የምንሰራው።

ስለሚያስቆጥሯቸው ጎሎች

“እንደሚታየው በድግግሞች የሰው ሜዳ እንጠጋለን ። ይሄም በልምምድ ስንሰራው የቆየነው ነው። እንደውም ከዚህ በላይ ኳሶችን እያመከንን ነው። ይህንን ለማስቀጠል ነው በተደጋጋሚ ስንሰራ የቆየነው ሁሉም ታክቲካል ዲሲፒሊንድ ስለነበሩ እርሱ ነው ትልቁ ውጤት።

ስለተፈጠረው ለውጥ

“እግርኳስ የሚታይ ስለሆነ ያየው ሰው ይፈርደዋል። አዲስ ነገር በቡድኑ ውስጥ መጣ የሚባለው በሚፈለገው መንገድ መጫወት ባለባቸው መጫወታቸው ነው። ታክቲካል ዲሲፒሊንድ መሆናቸው ፤ ይሄ ነው የቡድኑ ውጤት መንስኤ።

ስለየተጫዋች ቅያሪ

“እንዳያችሁት ከሆነ በአምስት ቢጫ የቡድኑ የመጀመርያ አጥቂ ቦታው ላይ አልነበረም። በሁለተኛ ያደረግነው አጥቂ በቦታው ትንሽ ድካም ሲመጣበት እዮብን ነው ከመስመር አውጥቼ የአጥቂ ባህሪ ስላለው እዚህ ላይ አደረኩት ያም ውጤት አምጥቷል እላለሁ።”

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ ከተማ

ስለተከታታይ ሽንፈት

” ቀድመን ጎሎችን አስቆጥረን ነበር ፤ አቅደነው የመጣነው ነገር አለ። በተለይ ከተጫዋቾች ጀርባ ያለውን ቦታ ለመጠቀም ጥረት አድርገናል። አጋጣሚዎችንም አልተጠቀምንም። ምንአልባት ቀድመን ነገሮችን የምንጨርስበት ዕድል ነበር። እንደዛም ሆኖ ጎል ተቆጥሮብናል። ያው ጥሩ ጊዜ እያሳለፍን አይደለም።

ክፍት ሜዳ ስለመፍቀዳቸው

“ምን አልባት ከአስሩ ልጆች ፊት ለፊት ላይ የመጀመርያው አጋማሽ ላይ የኳስ ሂደት ሊኖር ይችላል። በሁለተኛው አጋማሽ ግን በተወሰነ መልኩ የነበረውን የኳስ ቁጥጥር የመቆራረጥ ነገር ነበር።

ቡድኑን በምትፈልገው ደረጃ ስለመገኘቱ

“ያው ባለህ ነገር ነው የምትሰራው ፤ እጅህ ላይ ባለው ነገር። አሁን ላይ በሚፈለገው ደረጃ እየሄደ ነው ብዬ አላስብም። ግን መሻሻል፣ ማስተካከል አለብን።”