
ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሷል
ዛሬ ረፋድ ያለ ጎል ጨዋታውን ከወላይታ ድቻ ጋር ፈፅሞ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫዋች ተገቢነት ክስ ቀርቦበታል፡፡
የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታ ረፋድ 04፡00 ላይ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ ተገናኝተው ያለ ጎል ጨዋታቸውን መፈፀማቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ከደቂቃዎች በፊት የወላይታ ድቻ ክለብ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ከተጫዋች ተገቢነት ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለኝ በማለት ለፕሪምየር ሊጉ አወዳዳሪ አካል የቅሬታ ደብዳቤ ማስገባቱን የክለቡ ቡድን መሪ አቶ ዘላለም ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡
ክለቡ “ቅዱስ ጊዮርጊስ በጨዋታው ላይ ሦስት ጊዜ ብቻ አምስት ተጫዋቾችን መቀየር ሲኖርበት ክለቡ ይሄን ህግ በመጣስ ከዕረፍት በፊት ከነዓን ማርክነህን በሀይደር ሸረፋ ፣ ከዕረፍት መልስ ደስታ ደሙን በሱለይማን ሀሚድ ፣ ቡልቻ ሹራን በዳግማዊ አርአያ እና ጋቶች ፓኖምን በናትናኤል ዘለቀ በአራት የቅያሬ ጊዜ የለወጠበት ሂደት ከተቀመጠው ደንብ ውጪ በመሆኑ የጨዋታው ውጤት ይገባናል።” በማለት አቤቱታውን ማቅረቡን የቡድን መሪው ጨምረው ገልፀውልናል፡፡
ተዛማጅ ፅሁፎች
ሪፖርት | ፋሲል ከነማ የቅዱስ ጊዮርጊስን ያለመሸነፍ ጉዞ ገቷል
እጅግ ተጠባቂ በነበረው የዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ፋሲል ከነማ በኦኪኪ አፎላቢ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስን 1-0 በማሸነፍ የነጥብ ልዩነቱን ወደ አምስት ቀንሷል።...
የአሰልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 0-0 ወላይታ ድቻ
ያለጎል ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኃላ አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ- አርባምንጭ ከተማ ስለጨዋታው “የመጀመርያው አጋማሽ በተቻለ መልኩ ለማጥቃት ጥረት...
ሪፖርት | ፉክክር አልባው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
የግብ ሙከራዎች ባልነበሩበት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። አርባምንጭ ከተማዎች ሀዋሳን ከረታው ስብስብ ባደረጓቸው ሁለት...
ቅድመ ዳሰሳ | የ25ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች
ከነገዎቹ የሊጉ ጨዋታዎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚደረጉት ሁለት ጨዋታዎችን በዳሰሳችን ተመልክተናል። አዳማ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ ረፋድ ላይ የሚደረገው ጨዋታ ለተጋጣሚዎቹ...
ቅድመ ዳሰሳ | ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛ እና ሁለተኛ ቦታ ላይ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ እንደሚከተለው ቃኝተነዋል። የወቅቱ...
በሦስት ዳኞች ላይ ውሳኔ ተላልፏል
በወላይታ ድቻ እና በኢትዮጵያ ቡና ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩ ዳኞች ከፕሪምየር ሊጉ ውድድር ተሸኝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታ...