የሉሲዎቹ ዋና አሰልጣኝ ተጫዋቾችን ጠርተዋል

በዩጋንዳ ለሚደረገው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ23 ተጫዋቾችን ጥሪ አድርሷል፡፡

በዩጋንዳ ከግንቦት 24 ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ለሚደረገው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በቅርቡ በዋና አሰልጣኝነት የተሾሙት አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለውድድሩ የሚሆኑ 23 ተጫዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች መርጠዋል።

ከነገ ጀምሮም ወደ ዝግጅት የሚገባው የብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ከዚህ በታች ያለው መሆኑን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ግብ ጠባቂዎች

ታሪኳ በርገና (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ የምወድሽ ይርጋሸዋ (አዳማ ከተማ) ፣ ቤተልሄም ዮሐንስ (አዲስ አበባ ከተማ)

ተከላካዮች

ቤተልሄም በቀለ (መከላከያ) ፣
ብዙዓየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣
አሳቤ ሞሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣
ቅድስት ዘለቀ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ) ፣ ብርቄ አማረ (ድሬዳዋ ከተማ)

አማካዮች

ኝቦኝ የን (ኢትዮ ኤሌክትሪክ) ፣ እመቤት አዲሱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ገነት ኃይሉ (መከላከያ) ፣ መዓድን ሳሕሉ (መከላከያ) ፣ መሳይ ተመስገን (መከላከያ) ፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

አጥቂዎች

ረድኤት አስረሳኸኝ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ አረጋሽ ከልሳ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሎዛ አበራ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ረሒማ ዘርጋው (መከላከያ) ፣ ሴናፍ ዋቁማ (መከላከያ) ፣ አርየት ኦዶንግ (አዲስ አበባ ከተማ) ፣ ቱሪስት ለማ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ንግስት በቀለ (ቦሌ ክፍለከተማ)