የአሰልጣኞች አስተያየት | መከላከያ 1-2 ፋሲል ከነማ

ፋሲል ከነማ በቀትሩ ጨዋታ መከላከያን ከረታ በኋላ አሰልጣኞቹ አስተያየታቸውን አጋርተዋል።

አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ- ፋሲል ከነማ

ስለጨዋታው

“ወደ ፊት ለመጠጋት በምትጫወትበት ሰዓት እይንዳንዱ ጨዋታ ወሳኝ ነው። ጨዋታው ከባድ ሊሆን እንደሚችል ተናግሬአለው ፤ በጣም ፈታኝ ነበር።

የሙጂብ ቃሲም ያልተለመደ ሚና

“ሙጂብ ከዚህ በፊት የነበረበት ቦታ ስለሆነ የሚከብደው አይደለም። ልጆች በቅጣት እና በህመም ስታጣ ያለህ አማራጭ ይሄ ነው። ስለዚህ እሱን ነው ያለፉት ሦስት ቀናት ልምምድ ስንሰራ የነበረው ፤ ገብቶም ጥሩ ነገር ነው ያደረገው። በጣም ደስተኛ ነኝ

ስለዳኝነቱ

“ስለ ዳኝነት ማውራት አልፈልግም። መጀመርያ የተከሰቱ ነገሮች ጨዋታውን ቀይረውታል። ግን እኛ ጎል ማስቆጠራችን ወደ ጨዋታው እንድንመለስ አድርጎናል እንጂ ሞራል የሚገል ነገር ነበር።

ከመሪው ጋር ስለሚኖረው ጨዋታ

“ከዚህ በፊት ለተጋጣሚ የምንሰጠውን ክብር ሰጥተን እንገባለን። ተዘጋጅተን ሦስት ነጥብ ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን።”

አሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ -መከላከያ

ስለጨዋታው

“ከመቼውም ጊዜ በላይ በጣም ደስ ያለኝ ጨዋታነው። በሚፈለገው መጠን ሜዳ ላይ ልጆቹ መስዋዕት አድርገው ነው የወጡት። ልጆቹን ላመሰግን እወዳለሁ። በቀጣይ ጨዋታ ከዚህ በተሻለ ለየት ብለን እንደምንመጣ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለው።

ተጨማሪ ጎል ለማስቆጠር መቸገር

“ዝም ብለህ ጎል አታገባም። አንደኛ ተከላካይ ሰብረህ ነው የምትሄደው። ሁለተኛ ተከላክለህ ልታገባ የምትፈልግበት መንገድ ጥንቃቄ የተሞላው መሆን አለበት። ዝም ብለህ በአጋጣሚ አይደለም ጎል የሚገባው። ስለዚህ ዛሬ ከትልቅ ክለብ ጋር እንደመጫወታችን ከሚገባው በላይ ደስተኛ ነኝ። እንደውም ከዚህ በኋላ ለቡድኖች አስቸጋሪ ሆነን እንመጣለን።

ስለተጫዋቾቹ ጥረት
“ በትክክል ከሚገባው በላይ ደስተኛ ነኝ ፤ የሚገባውን አድርገዋል። በእግርኳስ ስህተትይኖራል። በጥቃቅን ኳስ ጎል ሊገባ ይችላል። ግን በዛሬው ጨዋታ በጥሩ ሁኔታ ተጫውተውታል።”

ያጋሩ