የአሰልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 0-0 ወላይታ ድቻ

ያለጎል ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኃላ አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል። 

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ- አርባምንጭ ከተማ

ስለጨዋታው

“የመጀመርያው አጋማሽ በተቻለ መልኩ ለማጥቃት ጥረት አድርገናል። በሁለተኛው በተወሰነ መልኩእነርሱ መጀመርያ ከነበራቸው አጨዋወት በመቀየር ዞናል አድርገዋል። ለእኛ ተከላካዮች ጊዜ አግኝተው ነበር። በተለይ መጨረሻ አካባቢ የጎል አጋጣሚ ለመፍጠር ጥረት ብናደርገም፣ ለማንኛውም አንዷ ነጥብ የተወሰነ ደረጃ ታሻሽላለች።

ስለአጨዋወት መንገዱ

“አራት አራት ሁለት የእኛ መስመሮች ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ጥቅጥቅ ያለ ነው። ማንም ቡድን እየገባ ማጥቃት አይችልም። ስለዚህ የሚታዮት የመስመር አጥቂዎች የመስመር ተከላካዮችም ናቸው። ወደ ኋላ እየተመለሱ እንዲያግዙ ወደፊት በመሄድ ልናጠቃ ነው የተነጋገርነው።

ስለማጥቃት ሽግግር

“በተለይ ማጥቃት ላይ መጨመር ያሉብን ነገሮች አሉ ግን በሁለት ጨዋታ ላይ የኳስ ቁጥጥራችን ከፍ ያለ ነው። ኳስ ተቆጣጥረን ለመጫወት አስበናል። ያው እኔ በቶታል ፉትቦል ነው የማምነው።”

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም -ወላይታ ድቻ

ስለአንዷ ነጥብ

“ከነጥቡ በፊት ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ተጫውተህ ከዚህ የበለጠ ኳስ መጠበቅ ከባድ ነው ብዬ አስባለው። ያም ቢሆን ቀላል ፉክክር አልነበረም። ትልቁ ነገር ስንታየው ወደ ትክክለኛው አቋም ሲመጣ በጎል በኩል ያለብንን ድርቀት ይመልስልናል ብለን እናስባለን። በጎን ቃልኪዳን እና ምንይሉ ቢኖሩ የተሻለ ይሆን ነበር። በአጠቃላይተመጣጣኝ ፉክክር፣ ሊጉ ላይ በከፍተኛ ፍላጎት የሚጫወቱ ቡድኖች የተገናኙበት ነው። ከነበረው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ውጤቱ ተገቢ ነው።

መስመሩን ለመስበር ስለተደረገ ጥረት

“እኛ ካለን የተጫዋች ስብስብ የራሳችን ታክቲክ ነበረን፣ አርባምንጭ ከተማን አታቀውም መቼ እንደሚያጠቃ እየቆየ የሚያጠቃ ስለሆነ በተቻለ መጠን የአየር ላይ ኳሳቸውን ለመቆጣጠር ሞክረናል፣ በተረፈ የእኛ ተጫዋቾች ሜዳ ላይ ስላደረጉት ነገር ሳላመሰግን አላልፍም።

ስለስንታየው መንግስቱ

“እንደ አጠቃላይ የቡድኔን ውስጡን ከእኔ በላይ የማቀው ሰው የለም። ስለዚህ በማጥቃትም በመከላከልም የትኛው ነው የሚያወጣን በማለት የሄድን ነው ያለነው። ያመቱ አካሄዳችን በቀላሉ ጎል የማይገባበት፣ የቡድናችን ስነ ልቦና የሚጠብቅ ውጤት እያደረግን ያለነው። በምንፈልገው መንገድ እያጠቃን ነው ብዬ አላስብም። እስከ 25ኛው ሳምንት የመጣንበት መንገድ አዋጥቶናል፣ ከዚህ በኋላ በዕረፍት በማጥቃት ላይ የምናስተካክለው ይኖራል።”

ያጋሩ