
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊያደርግ ነው
የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከፊቱ ያሉበት ዋልያው በሁለት ቀናት ልዩነት ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች ያደርጋል።
በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2023 በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የአህጉሪቱ ትልቅ ውድድር ለመብቃት የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ለማድረግ በዛሬው ዕለት ዝግጅት ጀምሯል። ከሜዳ ውጪ ለሚደረጉት ሁለት የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ከሚደረገው ልምምድ በተጨማሪ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ፌዴሬሽኑ እንቅስቃሴ ላይ የነበረ ሲሆን ውጥኑ እንደተሳካ ይፋ ሆኗል።
ፌዴሬሽኑ በድረ-ገፁ ባጋራው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከሌሶቶ ጋር የመጀመሪያውን ጨዋታ ግንቦት 20 ሲያደርግ ቀጣዩን ጨዋታ ደግሞ በተመሳሳይ ከሌሶቶ ጋር ከሁለት ቀናት በኋላ እንደሚያከናውን ተጠቁሟል። ሁለቱ ጨዋታዎች በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እንደሚደረጉም ታውቋል።
ተዛማጅ ፅሁፎች
ዋልያዎቹ ፈርዖኖቹን አንበርክከዋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታው ማላዊ ላይ ግብፅን ገጥሞ ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር 2-0 መርታት ችሏል።...
የዋልያዎቹ እና ፈረኦኖቹን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል
ነገ ምሽት በኢትዮጵያ እና ግብፅ መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ የሚመሩ አልቢትሮች ታውቀዋል። የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ነገም ሲቀጥሉ በምድብ...
የዋልያዎቹ አሠልጣኝ እና አምበል ከወሳኙ ጨዋታ በፊት ሀሳብ ሰጥተዋል
👉"የሳላ መኖር እና አለመኖር የእኛ እቅድ ላይ ምንም ተፅዕኖ አያደርግም" ውበቱ አባተ 👉"ከምድባችን ለማለፍ በምናደርገው ጉዞ የነገው ጨዋታ ወሳኝ ነው"...
ሱራፌል ዳኛቸው ለነገው ጨዋታ ይደርስ ይሆን ?
ነገ ምሽት የግብፅ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካዩን ሊያጣ ይችላል። የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታዎች በአህጉራችን የተለያዩ...
“ዓላማችን ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ መሳተፍ ነው” አቡበከር ናስር
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወሳኝ አጥቂ የሆነው አቡበከር ናስር ከነገው ጨዋታ በፊት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ...
የዋልያዎቹ አሰልጣኝ እና አምበል ከነገው ጨዋታ በፊት አስተያየት ሰጥተዋል
ዋልያዎቹ ነገ ከማላዊ ጋር የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ሲጠበቅ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ ከመገናኛ ብዙሀን...