የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የሚደረግበት ከተማ እና ቀን ታውቋል

የ2014 የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በሁለቱም ፆታዎች የሚደረግበት ቦታ እና ቀን ይፋ ሆነ፡፡

የ2014 የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በሀዋሳ ከተማ እንዲደረግ መወሰኑን ፌድሬሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ውድድሩን አስተናግዳ የነበረችሁ ሀዋሳ ዳግም ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ ውድድሩን የማስተናገድ ዕድል ተሰጥቷታል፡፡

በ2015 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የሚሳተፉ እና በተመሳሳይ ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የሚያድጉ ክለቦችን የሚለየው የሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዘንድሮው ውድድር ከሰኔ 18 ጀምሮ ሊደረግ ቀነ ቀጠሮ መቆረጡም ጭምር ይፋ ሆኗል፡፡

በውድድሩ ላይ ክልሎች እና ከተማ መስተዳደሮች በውስጥ ውድድሮቻቸው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁ ክለቦች ብቻ በውድድሩ ላይ እንደሚካፈሉ ተገልጿል፡፡

ያጋሩ