የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች

በሳምንቱ መጨረሻ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በሜዳዋ የምታስተናግደው ማላዊ የመጨረሻ ስብስቧን አሳውቃለች።

በ2023 በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት በሚከናወነው የአህጉሩ ትልቁ የሀገራት የውድድር መድረክ ላይ ለመሳተፍ በ12 ምድብ የተመደቡት ብሔራዊ ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን ከቀናት በኋላ ማድረግ ይጀምራሉ። በምድብ አራት ከማላዊ፣ ግብፅ እና ጊኒ ጋር የተመደበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ለምድብ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ዝግጅቱን እያከናወነ ይገኛል። የዋልያው የመጀመሪያ ተጋጣሚ የሆነችው ማላዊም ከቀናት በፊት ዝግጅቷን ጀምራ የነበረ ሲሆን ትናንት አመሻሽ ደግሞ ለጨዋታዎቹ የመጨረሻ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች።

የቡድኑ ዋና አለቃ ሩሜኒያዊው አሠልጣኝ ማሪዮ ማሪኒካ ሊሎንግዌ እና ኮናክሪ ላይ ኢትዮጵያ እና ጊኒን የሚገጥመውን የ25 ተጫዋቾች ዝርዝር ሲያሳውቁ የወሳኝ አምበላቸው ሊምቢካኒ ምዛቫ ስም አለመኖር ትኩረትን ስቧል። እርግጥ የብሎም ፎንቴ ሴልቲክ እና ጎልደን አሮንስ ተከላካይ ሀገሩ ማላዊ ከዚምባቡዌ ጋር በካሜሩኑ አፍሪካ ዋንጫ ስትጫወት ካስተናገደው የጡንቻ ጉዳት አለማገገሙን የሀገሪቱ የብዙሃን መገናኛዎች እየዘገቡ ይገኛሉ። ከተከላካዩ ውጪ በአፍሪካ ዋንጫው የነበሩት አጥቂው ሪቻርድ ሙቡሉ፣ የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ሮቢን ንግላንዴ፣ ዊሊያም ቶሌ እና ፒተር ቾሎፒም አለመመረጣቸው እያነጋገረ ይገኛል።

ከጥቂት ተጫዋቾች በስተቀር አብዛኛው በ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈውን ስብስብ ያካተቱት አሠልጣኝ ማሪዮ ማሪኒካ አንጋፋውን እና ከ2019 በኋላ በብሔራዊ ቡድኑ ቦታ ያልነበረውን አጥቂ ቹኬፖ ሙሶዎያ በመጨረሻ ዝርዝራቸው መካተታቸው ታውቋል።

ነበልባሎቹ በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩት ማላዊዎች መቀመጫቸውን ሊሎንግዌ አድርገው በቢሾፕ ማኬንዚ ስፖርት ኮምፕሌክስ ልምምዳቸውን በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን በአማዙሉ ከሚጫወተው አጥቂው ጋባዲንሆ ምሀንጎ ውጪ የመረጧቸውን ከሀገር ውጪ የሚጫወቱ ሁሉንም ተጫዋቾች ማግኘታቸው ተመላክቷል።

የተመረጡት ተጫዋቾች ዝርዝር :-