አምስት ተጫዋቾች ከብሔራዊ ቡድኑ ተቀንሰዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስት ተጫዋቾችን በመቀነስ የመጨረሻ ስብስቡን ለይቷል።

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት በሚከናወነው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የአህጉሩ ብሔራዊ ቡድኖች ከቀናት በኋላ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ማድረግ ይጀምራሉ። በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከማላዊ እና ግብፅ ጋር ላለበት የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን በሁለት ቀናት ልዩነትም ከሌሶቶ አቻው ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን አድርጎ አቻ ተለያይቷል።

በዝግጅቱ 28 ተጫዋቾችን ይዞ የነበረው ቡድኑ ዛሬ ረፋድ አምስት ተጫዋቾችን እንደቀነሰ ሶከር ኢትዮጵያ ከደቂቃዎች በፊት በጀመረው የልምምድ መርሐ-ግብር ተገኝታ አረጋግጣለች። በዚህም የግብ ዘቡ ሰዒድ ሀብታሙ፣ ተከላካዩ ብርሃኑ በቀለ፣ አማካዮቹ ቢኒያም በላይ እና ወንድማገኝ ኃይሉ እንዲሁም አጥቂው ሐብታሙ ታደሰ እንደተቀነሱ አውቀናል።

ከታች የተጠቀሱት ቀሪዎቹ 23 ተጫዋቾች ሦስት የልምምድ መርሐ-ግብሮችን በሀገር ውስጥ ካከናወኑ በኋላ የፊታችን ዓርብ ወደ ማላዊ ሊሎንግዌ እንደሚያመሩ ታውቋል።

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገብረሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ) ፣ በረከት አማረ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ዳግም ተፈራ (ሀዋሳ ከተማ)

ተከላካዮች

አስራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከተማ)፣ ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሱሌይማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ያሬድ ባዬ (ፋሲል ከነማ)፣ ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና)፣ ሚሊዮን ሰለሞን (አዳማ ከተማ)

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)፣ በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ)፣ መስዑድ መሐመድ (ጅማ አባ ጅፋር)፣ ሽመልስ በቀለ (ኤል ጎውና)

አጥቂዎች

አማኑኤል ገብረሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ቸርነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ዳዋ ሆቴሳ (አዳማ ከተማ)፣ በረከት ደስታ (ፋሲል ከነማ)፣ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና)