
አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ወደ ዩጋንዳ ጉዞ ጀምረዋል
ለሴቶች የሴካፋ ዋንጫ ተሳትፎ ትናንት ከቡድኑ ጋር ያልተጓዙት አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ወደ ዩጋንዳ ጉዞ ጀምረዋል።
ዛሬ በይፋ በጀመረው የሴካፋ የሴቶች ውድድር ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ትናንት ወደ ስፍራው ማቅናቱ ይታወሳል።
ታዲያ ዋና አሰልጣኙ ፍሬው ኃይለገብርኤል ከልዑካን ቡድኑ ጋር አብረው አለመጓዛቸውን ከሰዓታት በፊት መዘገባችን ይታወሳል። አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ማምሻውን ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሆነ በግል ጉዳይ ምክንያት እንዳልተጓዙ እና አሁን ወደ ዩጋንዳ ለማቅናት መሳፈራቸውን በመግለፅ ነገ ማለዳ ቡድኑን በመቀላቀል በከሰዓቱ ጨዋታ ቡድኑን እንደሚመሩ አረጋግጠውልናል።
ሉሲዎቹ ነገ የመጀመርያውን የምድብ ጨዋታቸውን ከዛንዚባር ጋር ቀትር 07:00 ላይ የሚያደርጉ ይሆናል።
ተዛማጅ ፅሁፎች
ሉሲዎቹ የሴካፋን ውድድፍ በሦስተኝነት አጠናቀዋል
በሴቶች የሴካፋ ዋንጫ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን 2ለ1 በመርታት የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ የሉሲዎቹ አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል በ4-3-3 የተጫዋች አደራደር ቅርፅ በዩጋንዳ...
ሉሲዎቹ በሴካፋ ውድድር ወደ ፍፃሜ ሳያልፉ ቀርተዋል
መቶ ሀያ ደቂቃዎችን የፈጀው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዩጋንዳን አሸናፊ በማድረግ ተጠናቋል። ለፍፃሜ የሚያልፈውን ቡድን ለመለየት ስድስት ሰዓት...
ሉሲዎቹ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል
በሴካፋ ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የምድቡ ሁለተኛ ሆኖ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል። በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ስምንት ብሔራዊ...
ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ጋር ነጥብ ተጋርታለች
በሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ያደረጉት ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ 2-2 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ሉሲዎቹ ዛንዚባርን በጎል ተንበሽብሸው ሲረቱ ከተጠቀሙት...
ሉሲዎቹ የሴካፋ ዋንጫን በድል ጀምረዋል
በሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በመጀመሪያ ጨዋታው ዛንዚባርን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 5-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በምድብ ሁለት የሚገኙትን ኢትዮጵያ እና ዛንዚባርን...
አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ዩጋንዳ አይገኙም
በሴካፋ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን የሚመሩት አሠልጣኝ ፍሬው በአሁኑ ሰዓት ከስብስቡ ጋር እንደማይገኙ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። የምስራቅ እና...