የአሠልጣኞች አስተያየት | ሰበታ ከተማ 0-0 ሀዲያ ሆሳዕና

ያለግብ አቻ ከተጠናቀቀው የሰበታ እና ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ በኋላ አሠልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

ብርሃን ደበሌ – ሰበታ ከተማ

ጨዋታው እንዴት ነበር…?

ሦስት ነጥብ ይገባን ነበር። ይሄንን ጨዋታ ማሸነፍ ይገባን ነበር። ነገርግን የምፈልገውን ከጨዋታው አላገኘሁም።

ስለጥንቃቄ አዘል የአጨዋወት መንገዳቸው…?

እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ጥንቃቄ አዘል አጨዋወት እየተጫወትን ነበር። በመሐል በመሐል የጎል ማግባት ሙከራ ያደረግንበት መንገድ ደከም በማለቱ ጎል ሳናስቆጥር ወጥተናል።

ስለሁለተኛው አጋማሽ ብቃት…?

አማካይ መስመሩ ላይ ተጫዋቾችን አብዝተን ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የመስመር ተጫዋቾቹን በከፍተኛ ፍጥነት እንጠቀማለን ብለን ነበር። ነገርግን አልተሳካም።

በአንድ ወር ውስጥ 3 የተሟላ ልምምድ አድርገው ጨዋታዎችን በጥሩ ሁኔታ እየቀረቡ ስላለበት መንገድ…?

በመነጋገር እግር ኳሱ የሚፈልገውን ነገር ሜዳ እስገገባን ድረስ እናድርግ የሚለውን ተጫዋቾቹ ላይ ለማስረፅ በመሞከር እነሱም ሜዳ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ለመከወን በቁ እንጂ ባለው ውስብስብ ነገር ሁሉም ውስጡ ተጎድቷል።

ስለቀጣይ ጨዋታዎች…?

ይሄ ውጤት እግር ኳስ መጨረሻ እንዳልሆነ ነው ያሳየን። ብንሸነፍ ወደ ታች እንሄድ ነበር። ሦስቱን ቀሪ ጨዋታዎች ብናሸንፍ ደግሞ የሚፈጠረው አይታወቀወም። እግር ኳስ ተስፋ አይቆረጥበትም። ተግቶ ሰርቶ የሚመጣውን በፀጋ መቀበል ነው።

ሙሉጌታ ምህረት – ሀዲያ ሆሳዕና

ጨዋታው እንደለት ነበር…?

ከሞላ ጎደል ያሰብነውን ለማሳካት የቀረን ማሸነፍ ብቻ ነበር። ሜዳ ላይ በነበረው እንቅስቃሴ ተጫዋቾቼ ጥሩ ነበሩ። የግብ እድሎችንም አግኝተዋል። የአጨራረስ ችግር ነው። እርሱን ማስተካከል ነው።

ከሰበተሰ ከተማ ስለገጠማቸው ፈተና…?

መጀመሪያም ተናግሬያለው። ታች ይሁኑ እንጂ ጠንካራ እና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች አሏቸው። ይህንን ተከትሎም እንደምንቸገር እናውቅ ነበር። ለዛም ነው ፈትነውን ያለቀው። ቢሆንም ግን አለመጠቀማችን ነው እንጂ እድሎችን አግኝተን ነበር።

ስለቀጣይ ጨዋታዎች…?

እንደዚሁ ይቀጥላል። እንዳለነው ይቀጥላለ። ነጥብ እስከምናገኝ ድረስ እንቀጥላለን። ምንም የተለየ ነገር የለም።

በዚህ ሳምንት ላለመውረድ የሚፎካከሩ ቡድኖች አለማሸነፋቸው…?

ከቡድኖች ጥንካሬ እና ጉጉት ነው የሚል እሳቤ ነው ያለኝ። አሸንፎ ለመውጣት ችኮላ ነው የሚታየው።