በአህመድ ሁሴን ብቸኛ ግብ አርባምንጭ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን ከረታበት ጨዋታ በኋላ አሠልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል።
መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ ከተማ
ስለተከታታይ ሦስተኛ ድሉ…?
በመጀመሪያ ፈጣሪዬን ማመስገን እፈልጋለው። እንደሚታየው ብዙ ነገሮችን ለመለወጥ ጥረናል። የታገሰ አመራር ነበር። ባይታገሱ ኖሮ ይሄንን ላናይ እንችል ነበር። በዚህ አጋጣሚ አመራሮቹን ማመስገን እፈልጋለው። ስራው ትዕግስት ይፈልጋል። ስንከላለል ጠንካራ ነገር ይታያል። በቀላሉ እጅ አንሰጥም። ሰው ሜዳም ሄደን መጫን፣ በሜዳችንም መከላከል፣ ኳስ መቆጠቀጠር እና ጎል ማስቆጠር እንችላለን። ይሄንን ሊያሟላ የሚችል ነገር ለመስራት ጥረት አድርገናል። ቤታችን ተሰርቷል ብዬ አስባለው።
ስለእንዳልካቸው እና አህመድ ጥምረት…?
የአህመድ መጎዳት ነበር። ቅድም ተናግሬያለው። ሀገርን እግዚያብሄር ካልጠበቀ እና ቤትን ካልሰራ ከባድ ነው የሚሆነው። አንዳንዴ እኔ ሰራው ባልልም ነገሮች ይሰካካል። በተወሰነ መልሉ ፈጠራ ለመጨመር እንዳለን ወደ ፊት አድርገናል። አህመድ ደግሞ ከጉዳት ሲመለስ ነገሮች በደንብ አድርገው ነው የመጡት። ተከታታይ እንዳለ ብዙ ኳሶችን አሲስት እያደረገ ነው። አህመድም እንደዛው። ስለዚህ ጥሩ ቅንጅት ነው እያየን ያለነው።
ካፓይቶ ከተጎዳ በኋላ ፀጋዬ ስለገባበት መንገድ…?
ቡድኑን ካሳደገው አንዱ ካፓይቶ ነው። ፀጋዬም ብቃት ያለው ተጫዋች ነው። ለየት የሚለው አንድ ነገር እኛ ጋር ያሉት የሚተኩት ተጫዋቾች ከቀዳሚዎቹ ጋር ተመሳሳይ ነገር ነው ያላቸው። ይሄ አንዱ ጥሩ ነገር ነው።
ካሣዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና
ጨዋታው እንዴት ነበር…?
ጥሩ ነበር። እነሱ ተከማችተው ሲዘጉ የተከፈቱ ቦታዎችን ተጠቅመን የጎል እድል ብዙ መፍጠር አልቻልንም። የተፈጠሩ የጎል ዕድሎች አሉ። ሌላው በተለይ ከእረፍት በፊት እነርሱ ብዙ እንዲጫወቱ ዕድል የመስጠት ነገር ነበር። ከእረፍት በኋላ እንኳን ታርሟል። በአጠቃላይ የነበረው ነገርግን ጥሩ ነው።
በተጋጣሚ በኩል ስለነበረው አጨዋወት…?
ከእረፍት በፊት የሚጣሉት ኳሶች ብዙ አስቸጋሪ አልነበሩም። ኋላ ያሉት ተጫዋቾች ቅርፃቸውን በመጠበቅ መቆጠቀጠር ተችሏል። በዚህ አይነት መልኩ ስለሚመጡ ማለት ነው። የተቆጠረብን ጎል ብዙ እንዲጫወቱ እና የእኛን ሰዎች እንዲቆጣጠሩ እንድል አለመስጠት ነበር። ከእረፍት በኋላ ያንን በተሻለ ለማድረግ ሞክረናል። ከእረፍት በፊት ግን እንደሱ አይነት ክፍተቶች ነበሩ። ግብም ያስቆጠሩት ያንን ክፍተት ተጠቅመው ነው።